የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ቆሮንቶስ 3:1-15

1 ቆሮንቶስ 3:1-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ወድ​ሞች ሆይ፥ እኔስ የሥ​ጋና የደም እንደ መሆ​ና​ችሁ፥ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በማ​መን ሕፃ​ናት እንደ መሆ​ና​ችሁ እንጂ እንደ መን​ፈ​ሳ​ው​ያን ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ አል​ቻ​ል​ሁም። ወተ​ትን ጋት​ኋ​ችሁ፤ ጽኑ መብ​ልም ያበ​ላ​ኋ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ገና አል​ጠ​ነ​ከ​ራ​ች​ሁ​ምና፤ በሥ​ጋዊ ሕግም ትኖ​ራ​ላ​ች​ሁና እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ቃ​ኑና የም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከሆነ ግን ሥጋ​ው​ያን መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን? እንደ ሰው ልማ​ድስ የም​ት​ኖሩ መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን? ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ፥ “እኔ የጳ​ው​ሎስ ነኝ” የሚል አለና፤ ሌላ​ውም፥ “እኔ የአ​ጵ​ሎስ ነኝ” ቢል እና​ንተ ሥጋ​ው​ያን መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ግ​ዲህ ጳው​ሎስ ምን​ድን ነው? አጵ​ሎ​ስስ ምን​ድን ነው? እነ​ር​ሱስ በቃ​ላ​ቸው የአ​መ​ና​ችሁ አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠው ነው። እኔ ተከ​ልሁ፤ አጵ​ሎ​ስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ደገ። አሁ​ንም የሚ​ተ​ክ​ልም ቢሆን፥ የሚ​ያ​ጠ​ጣም ቢሆን የሚ​ጠ​ቅ​መው ነገር የለም፤ የሚ​ያ​ሳ​ድግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ። የሚ​ተ​ክ​ልም፥ የሚ​ያ​ጠ​ጣም አንድ ናቸው፤ ሁሉም እንደ ድካ​ማ​ቸው ዋጋ​ቸ​ውን ይቀ​በ​ላሉ። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ እን​ተ​ባ​በ​ራ​ለ​ንና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች ነንና፤ እና​ን​ተም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕንፃ ናችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልህ የጠ​ራ​ቢ​ዎች አለቃ ሆኜ እኔ መሠ​ረት ጣልሁ፤ ሌላ​ውም በእ​ርሱ ላይ ያን​ጻል፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ግን በእ​ርሱ ላይ እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያ​ንጽ ይጠ​ን​ቀቅ። ነገር ግን ከተ​መ​ሠ​ረ​ተው በቀር ሌላ መሠ​ረት ሊመ​ሠ​ርት የሚ​ችል የለም፤ መሠ​ረ​ቱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው። በዚህ መሠ​ረት ላይ በወ​ር​ቅና በብር፥ በከ​በረ ድን​ጋ​ይና በእ​ን​ጨት፥ በሣ​ርና በአ​ገዳ የሚ​ያ​ንጽ ቢኖ​ርም፥ የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሥራ ይገ​ለ​ጻል፤ እሳ​ትም በፈ​ተ​ነው ጊዜ ቀኑ ይገ​ል​ጠ​ዋል፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱ​ንም ሥራ እሳት ይፈ​ት​ነ​ዋል። ሥራው ጸንቶ የተ​ገ​ኘ​ለት ሰው ዋጋ​ውን የሚ​ቀ​በል እርሱ ነው። ሥራው የተ​ቃ​ጠ​ለ​በት ግን ዋጋ​ውን ያጣል፤ እር​ሱም ከእ​ሳት እን​ደ​ሚ​ድን ሰው ይድ​ናል።

1 ቆሮንቶስ 3:1-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ወንድሞች ሆይ፤ በክርስቶስ ገና ሕፃናት እንደ መሆናችሁ፣ እንደ ሥጋውያን እንጂ እንደ መንፈሳውያን ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ስላልጠነከራችሁ ወተት እንጂ ጠንካራ ምግብ አልመገብኋችሁም፤ አሁንም ቢሆን ገና ናችሁ። አሁንም ሥጋውያን ናችሁ፤ በመካከላችሁ ቅናትና ክርክር አለ። ታዲያ፣ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? ተግባራችሁስ እንደ ማንኛውም ሰው ተግባር መሆኑ አይደለምን? ምክንያቱም አንዱ፣ “እኔ የጳውሎስ ነኝ”፣ ሌላው ደግሞ፣ “እኔ የአጵሎስ ነኝ” ቢል፣ ሰብአዊ ፍጡር ብቻ መሆናችሁ አይደለምን? ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? ጌታ ለእያንዳንዳቸው በሰጣቸው መጠን የሚሠሩ አገልጋዮች ናቸው፤ እናንተም ወደ እምነት የመጣችሁት በእነርሱ አማካይነት ነው። እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስ ውሃ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ፣ የሚተክልም ሆነ ውሃ የሚያጠጣ ምንም አይደለም። የሚተክልም ሆነ የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን የራሱን ሽልማት ይቀበላል። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ዕርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ። ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ጸጋ መጠን፣ እንደ አንድ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልሁ፤ ሌላውም በላዩ ላይ ይገነባል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ እንዴት እንደሚገነባ መጠንቀቅ አለበት። ምክንያቱም አንድ ጊዜ ከተመሠረተው መሠረት በቀር ሌላ መሠረት መጣል የሚችል ማንም የለም፤ ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ወይም በብር፣ በከበረ ድንጋይ ወይም በዕንጨት፣ በሣር ወይም በአገዳ ቢያንጽ፣ ሥራው እንዴት እንደ ሆነ ይታያል፤ ምክንያቱም ያ ቀን ወደ ብርሃን ያመጣዋል። በእሳት ስለሚገለጥ እሳቱ የእያንዳንዱን ሰው ሥራ ምንነት ይፈትናል። ማንም የገነባው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል፤ ሥራው የተቃጠለበት ግን ሽልማት ይቀርበታል፤ እርሱ ራሱ ግን ይድናል፤ ይሁን እንጂ የሚድነው በእሳት ውስጥ በጭንቅ እንደሚያልፍ ሆኖ ነው።

1 ቆሮንቶስ 3:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤ ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? አንዱ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ ሁለተኛውም፦ እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን? አጵሎስ እንግዲህ ምንድር ነው? ጳውሎስስ ምንድር ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደ ሰጣቸው ያገለግላሉ። እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም። የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፥ ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል። የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ። ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።

1 ቆሮንቶስ 3:1-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ሳስተምራችሁ ሥጋውያንና በክርስቶስ ገና ያልጠነከራችሁ ሕፃናት እንደ መሆናችሁ መጠን ነው እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ መጠን አይደለም። ጠንካራ ምግብ መብላት እንደማይችሉ ሕፃናት ስለ ሆናችሁ እኔ የመገብኳችሁ ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም፤ አሁንም ቢሆን ጠንካራ ምግብ መመገብ ገና የማትችሉ ናችሁ። እናንተ አሁንም ገና ሥጋውያን ናችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ስለምትቀናኑና ስለምትከራከሩ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? የምትሠሩትስ እንደ ተራ ሰው አይደለምን? አንዱ “እኔ የጳውሎስ ነኝ” ሌላው ደግሞ “እኔ የአጵሎስ ነኝ” ሲል ተራ የዓለም ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን? ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? እነርሱ እናንተ እንድታምኑ ያደረጉአችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ እያንዳንዳቸው የሚያገለግሉትም ጌታ ለያንዳንዳቸው በመደበላቸው ሥራ ነው፤ እኔ ተከልኩ፤ አጵሎስ ውሃ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ለሥራው ዋና የሆነው ተክሉን ያሳደገው እግዚአብሔር ነው እንጂ የተከለም ሆነ ውሃ ያጠጣ ምንም አይደለም። የተከለም ሆነ ውሃ ያጠጣ እኩል ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይቀበላል። እኛ ለእግዚአብሔር አብረን የምንሠራ አገልጋዮች ነን፤ እናንተም የእግዚአብሔር እርሻና የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ። እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም እኔ በጣልኩት መሠረት ላይ ይገነባል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በዚያ ላይ እንዴት እንደሚገነባ መጠንቀቅ አለበት። አንድ ጊዜ ከተመሠረተው መሠረት በቀር ማንም ሌላ መሠረት መጣል አይችልም፤ ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ፥ ወይም በብር በከበረ ድንጋይ፥ ወይም በእንጨት፥ በሣር ወይም በገለባ የሚገነባ ቢኖር የእያንዳንዱ ሰው ሥራ የሚገለጥበት የፍርድ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ቀን የእያንዳንዱ ሰው ሥራ ምን ዐይነት እንደ ሆነ በእሳት ተፈትኖ ይገለጣል። አንድ ግንበኛ በመሠረቱ ላይ የሠራው ሥራ በእሳት ተፈትኖ ሳይጐዳ ጸንቶ ከቆመ ግንበኛው ዋጋውን ያገኛል። ሥራው በእሳት ተቃጥሎ የተደመሰሰበት ግንበኛ ግን ዋጋው ይቀርበታል፤ ይሁን እንጂ እርሱ ራሱ፥ በእሳት ውስጥ አልፎ ሳይቃጠል እንደሚቀር ሰው ይድናል።

1 ቆሮንቶስ 3:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ወንድሞች ሆይ! እኔም፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጠንካራ መብል ለመብላት አልቻላችሁም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ገና አትችሉም፤ እናንተ ገና ሥጋውያን ናችሁ፤ ቅናትና ጭቅጭቅ እስከተገኘባችሁ፥ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? አንዱ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤” ሌላው ደግሞ “እኔ የአጵሎስ ነኝ፤” ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን? አጵሎስ እንግዲህ ምንድነው? ጳውሎስስ ምንድነው? በእነርሱ በኩል ያመናችሁ፥ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደሰጣቸው፥ አገልጋዮች ናቸው፤ እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ እንግዲህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ሆነ ወይም የሚያጠጣ ቢሆን ምንም አይደለም። የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ክፍያ ይቀበላል። ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነንና፤ የእግዚአብሔር እርሻ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ። የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠኝ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም በዚያ ላይ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በዚያ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ። ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልም፤ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ፥ በብር፥ በከበሩ ድንጋዮች፥ በእንጨት፥ በሣር፥ በገለባ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ፥ ያ ቀን በገሃድ ያሳያልና፤ የእያንዳንዱም ሥራ ምን መሆኑን እሳቱ ራሱ ይፈትነዋል። ማንም በዚያ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፤ እርሱ ራሱ ግን ይድናል፤ ሆኖም ግን በእሳት አልፎ ይሆናል።