ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 3
3
ስለ መጀመሪያ ትምህርት
1ወድሞች ሆይ፥ እኔስ የሥጋና የደም እንደ መሆናችሁ፥ ክርስቶስንም በማመን ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ እንደ መንፈሳውያን ላስተምራችሁ አልቻልሁም። 2#ዕብ. 5፥12-13። ወተትን ጋትኋችሁ፤ ጽኑ መብልም ያበላኋችሁ አይደለም፤ ገና አልጠነከራችሁምና፤ 3በሥጋዊ ሕግም ትኖራላችሁና እርስ በርሳችሁ የምትቃኑና የምትከራከሩ ከሆነ ግን ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? እንደ ሰው ልማድስ የምትኖሩ መሆናችሁ አይደለምን? 4#1ቆሮ. 1፥12። ከመካከላችሁ፥ “እኔ የጳውሎስ ነኝ” የሚል አለና፤ ሌላውም፥ “እኔ የአጵሎስ ነኝ” ቢል እናንተ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? 5እንግዲህ ጳውሎስ ምንድን ነው? አጵሎስስ ምንድን ነው? እነርሱስ በቃላቸው የአመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ሰጠው ነው። 6#የሐዋ. 18፥4-11፤24-28። እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አሳደገ። 7አሁንም የሚተክልም ቢሆን፥ የሚያጠጣም ቢሆን የሚጠቅመው ነገር የለም፤ የሚያሳድግ እግዚአብሔር ነው እንጂ። 8የሚተክልም፥ የሚያጠጣም አንድ ናቸው፤ ሁሉም እንደ ድካማቸው ዋጋቸውን ይቀበላሉ። 9በእግዚአብሔር ሥራ እንተባበራለንና፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች#በግሪኩ “የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ” ይላል። ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።
10እግዚአብሔር እንደ ሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልህ የጠራቢዎች አለቃ ሆኜ እኔ መሠረት ጣልሁ፤ ሌላውም በእርሱ ላይ ያንጻል፤ እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ። 11ነገር ግን ከተመሠረተው በቀር ሌላ መሠረት ሊመሠርት የሚችል የለም፤ መሠረቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። 12በዚህ መሠረት ላይ በወርቅና በብር፥ በከበረ ድንጋይና በእንጨት፥ በሣርና በአገዳ የሚያንጽ ቢኖርም፥ 13የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጻል፤ እሳትም በፈተነው ጊዜ ቀኑ ይገልጠዋል፤ የእያንዳንዱንም ሥራ እሳት ይፈትነዋል። 14ሥራው ጸንቶ የተገኘለት ሰው ዋጋውን የሚቀበል እርሱ ነው። 15ሥራው የተቃጠለበት ግን ዋጋውን ያጣል፤ እርሱም ከእሳት እንደሚድን ሰው ይድናል።
16 #
1ቆሮ. 6፥19፤ 2ቆሮ. 6፥16። እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንፈስም በእናንተ ላይ አድሮ እንደሚኖር አታውቁምን? 17የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚያፈርሰውን ግን እርሱን ደግሞ እግዚአብሔር ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነውና፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም እናንተ ራሳችሁ ናችሁ፤ እንግዲያስ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አታርክሱ።#“እንግዲያስ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አታርክሱ” የሚለው በግሪኩ የለም።
18ራሳችሁን አታስቱ፤ ከመካከላችሁ በዚህ ዓለም ጥበበኛ እንደ ሆነ የሚያስብ ሰው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላዋቂ ያድርግ። 19#ኢዮብ 5፥13። የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ድንቍርና ነውና፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “ጠቢባንን የሚገታቸው ተንኰላቸው ነው።” 20ዳግመኛ “የጥበበኞች አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ያውቃል” ብሎአል።#መዝ. 93፥11። 21ስለዚህም እንግዲህ አንዱ ስንኳ በሰው አይመካ፤ ሁሉ የእናንተ ነውና። 22ጳውሎስም ቢሆን፥ አጵሎስም ቢሆን፥ ጴጥሮስም ቢሆን፥ ዓለምም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ ሞትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን ሁሉ የእናንተ ነው። 23እናንተ ግን የክርስቶስ ናችሁ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 3: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ