የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ቆሮንቶስ 15:1-20

1 ቆሮንቶስ 15:1-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንና የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ትን ያላ​ች​ሁ​በ​ትን፥ በእ​ር​ሱም የም​ት​ድ​ኑ​በ​ትን ወን​ጌል አሳ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ። ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁን ታስቡ እንደ ሆነ በቃሌ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያለ​ዚያ ግን ማመ​ና​ችሁ ከንቱ ነው። እኔ የተ​ማ​ር​ሁ​ትን አስ​ቀ​ድሜ መጽ​ሐፍ እን​ደ​ሚል እን​ዲህ ብዬ አስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ፥ “ክር​ስ​ቶስ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ሞተ። ተቀ​በረ፤ እንደ ተጻ​ፈም በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተነሣ።” ለጴ​ጥ​ሮስ ታየው፤ ከዚ​ህም በኋላ ለዐ​ሥራ አንዱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ታያ​ቸው። ከዚ​ህም በኋላ ከአ​ም​ስት መቶ ለሚ​በዙ ወን​ድ​ሞች በአ​ንድ ጊዜ ታያ​ቸው፤ ከእ​ነ​ርሱ ብዙ​ዎቹ እስከ ዛሬ አሉ፤ አን​ዳ​ን​ዶቹ ግን አን​ቀ​ላ​ፍ​ተ​ዋል። ከዚ​ህም በኋላ ለያ​ዕ​ቆብ ታየው፤ ኋላም ለሐ​ዋ​ር​ያት ሁሉ፤ ከሁ​ሉም በኋላ ጭን​ጋፍ ለም​መ​ስል ለእኔ ታየኝ። ከሐ​ዋ​ር​ያት ሁሉ እኔ አን​ሣ​ለ​ሁና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ስለ አሳ​ደ​ድሁ ሐዋ​ርያ ተብዬ ልጠራ የማ​ይ​ገ​ባኝ፥ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም። አሁ​ንም እኔም ብሆን፥ እነ​ር​ሱም ቢሆኑ እን​ዲህ እና​ስ​ተ​ም​ራ​ለን፤ እና​ን​ተም እን​ዲሁ አም​ና​ች​ኋል። ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ተነ​ሥ​ቶ​አል ብለን ለሌ​ላው የም​ና​ስ​ተ​ምር ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ሙታን አይ​ነ​ሡም የሚሉ እን​ዴት ይኖ​ራሉ? ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ አል​ተ​ነ​ሣማ፤ ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ካል​ተ​ነሣ እን​ግ​ዲ​ያስ ትም​ህ​ር​ታ​ችን ከንቱ ነው፤ የእ​ና​ን​ተም እም​ነ​ታ​ችሁ ከንቱ ነው። እኛም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮች ሆነ​ናል፤ ክር​ስ​ቶ​ስን አስ​ነ​ሣው ብለ​ና​ልና፥ እን​ግ​ዲያ ሳያ​ስ​ነ​ሣው ነውን?። ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን አል​ተ​ነ​ሣማ። ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ካል​ተ​ነሣ ማመ​ና​ችሁ ከንቱ ነው፤ ገናም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ አላ​ችሁ። እን​ግ​ዲ​ያስ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነው የሞቱ ጠፍ​ተ​ዋላ። በዚህ ዓለም ሕይ​ወት ብቻ ክር​ስ​ቶ​ስን ተስፋ ከአ​ደ​ረ​ግ​ነው ከሰው ሁሉ ይልቅ ጉዳ​ተ​ኞች ነን። አሁ​ንም ክር​ስ​ቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አል።

1 ቆሮንቶስ 15:1-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አሁንም ወንድሞች ሆይ፤ የሰበክሁላችሁንና የተቀበላችሁትን፣ ደግሞም ጸንታችሁ የቆማችሁበትን ወንጌል ላሳስባችሁ እወድዳለሁ፤ የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣ በዚህ ወንጌል ትድናላችሁ፤ አለዚያ ያመናችሁት በከንቱ ነው። እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤ ከዚያም ለኬፋ ታየ፤ ቀጥሎም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ፤ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነዚህም አብዛኛዎቹ በሕይወት አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን አንቀላፍተዋል። ከዚያም ለያዕቆብ ታየ፤ በኋላም ለሐዋርያት በሙሉ ታየ፤ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምቈጠር ለእኔ ደግሞ ታየ። እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ፣ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ እንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን አሳድጃለሁ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ እንዲያውም ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ዳሩ ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። እንግዲህ እኔም ሆንሁ እነርሱ የምንሰብከው ይህንኑ ነው፤ እናንተም ያመናችሁት ይህንኑ ነው። ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ፣ ከእናንተ አንዳንዶቹ እንዴት የሙታን ትንሣኤ የለም ይላሉ? የሙታን ትንሣኤ ከሌለማ ክርስቶስም አልተነሣም ማለት ነዋ! ክርስቶስም ካልተነሣ ስብከታችን ዋጋ ቢስ ነው፤ እምነታችሁም ከንቱ ነው። ከዚህም በላይ፣ እግዚአብሔር ክርስቶስን ከሞት አስነሥቶታል ብለን በመመስከራችን፣ ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን የማይነሡ ከሆነ፣ ክርስቶስንም አላስነሣውም ማለት ነው፤ ምክንያቱም ሙታን ካልተነሡ፣ ክርስቶስም አልተነሣም። ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም እስከ አሁን ድረስ ከነኀጢአታችሁ አላችሁ ማለት ነው። እንዲህም ከሆነ፣ በክርስቶስ ያንቀላፉት ጠፍተዋል ማለት ነው። ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለዚህች ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን። ነገር ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵራት ሆኖ በርግጥ ከሙታን ተነሥቷል።

1 ቆሮንቶስ 15:1-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤ በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ። እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ። እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። እንግዲህስ እኔ ብሆን እነርሱም ቢሆኑ እንዲሁ እንሰብካለን እንዲሁም አመናችሁ። ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ፦ ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ? ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ፤ ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤ ደግሞም፦ ክርስቶስን አስነሥቶታል ብለን በእግዚአብሔር ላይ ስለ መሰከርን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን ግን የማይነሡ ከሆነ እርሱን አላስነሣውም። ሙታን የማይነሡ ከሆነ ክርስቶስ አልተነሣማ፤ ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ። እንግዲያስ በክርስቶስ ያንቀላፉት ደግሞ ጠፍተዋላ። በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን። አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።

1 ቆሮንቶስ 15:1-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አሁን ደግሞ ወንድሞች ሆይ! ያስተማርኳችሁን የወንጌል ቃል ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ፤ ይህም የወንጌል ቃል እናንተ የተቀበላችሁትና ጸንታችሁ የቆማችሁበት ነው። እኔ ያስተማርኳችሁን የወንጌል ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ በእርሱ ትድናላችሁ፤ አለበለዚያ ግን ያመናችሁት በከንቱ ነው። እኔ የተቀበልኩትን በመጀመሪያ ደረጃ ያለውን ነገር ለእናንተ አስተላለፍኩላችሁ፤ ያስተላለፍኩላችሁም ነገር በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈው ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ከሞት ተነሣ የሚል ነው። እርሱ ለጴጥሮስ ታየ፤ ኋላም ለዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ታየ፤ ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ተከታዮቹም በአንድ ጊዜ ታያቸው፤ ከእነርሱ አብዛኞቹ እስከ አሁን በሕይወት አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ሞተዋል። ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ታየ፤ ለሐዋርያትም ሁሉ ታያቸው። በመጨረሻም እንደ ጭንጋፍ ለሆንኩት ለእኔ ደግሞ ታየኝ። እኔ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያሳደድኩ ስለ ሆነ ከሐዋርያት ሁሉ ያነስኩና ሐዋርያም ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነኝ። ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። እንግዲህ እኔም ሆንኩ እነርሱ የምናስተምረው ይህንኑ ነው፤ እናንተም ያመናችሁት ይህንኑ ነው። ነገር ግን ክርስቶስ ከሞት እንደ ተነሣ የምናስተምር ከሆነ ከእናንተ አንዳንዶቹ ከሞት መነሣት የለም እንዴት ይላሉ? ከሞት መነሣት ከሌለ ክርስቶስ ከሞት አልተነሣም ማለት ነው፤ ክርስቶስ ከሞት ካልተነሣ የእኛም ትምህርት ሆነ የእናንተም እምነት ከንቱ መሆኑ ነው፤ ደግሞም እግዚአብሔር ክርስቶስን ከሞት አስነሥቶታል ብለን በማስተማራችን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነናል ማለት ነው፤ እንግዲህ የሞቱት ሰዎች ከሞት ካልተነሡ እግዚአብሔር ክርስቶስንም ከሞት አላስነሣውም ማለት ነው። የሞቱት ሰዎች ከሞት ካልተነሡ ክርስቶስም ከሞት አልተነሣም ማለት ነው። ክርስቶስ ከሞት ያልተነሣ ከሆነ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ ገና በኃጢአታችሁ ውስጥ ትኖራላችሁ ማለት ነው፤ በክርስቶስ አምነው የሞቱት ጠፍተዋል ማለት ነው፤ በክርስቶስ ተስፋ የምናደርገው ለዚህ ዓለም ሕይወት ብቻ ከሆነ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የሚታዘንልን መሆናችን ነው፤ ነገር ግን ክርስቶስ ለሞቱት ከሞት የመነሣት በኲር ሆኖ በእርግጥ ከሞት ተነሥቶአል።

1 ቆሮንቶስ 15:1-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ወንድሞች ሆይ! አሁን የሰበክሁላችሁንና የተቀበላችሁትን ደግሞም ጸንታችሁ የቆማችሁበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤ የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፥ ያመናችሁት በከንቱ ካልሆነ በስተቀር፥ የምትድኑበትን ወንጌል ነው። እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ለኀጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤ ከዚያም ለኬፋ ታየ፤ ቀጥሎም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ፤ ከዚያም በኋላም ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነዚህም አብዛኛዎቹ እስካሁን በሕይወት አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን አንቀላፍተዋል። ከዚያም ለያዕቆብ ታየ፤ በኋላም ለሐዋርያት በሙሉ ታየ፤ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምቆጠር ለእኔ ደግሞ ታየ። እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ፥ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ እንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን አሳድጃለሁ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። እንግዲህ እኔም ሆንሁ እነርሱ የምንሰብከው፤ እናንተም ያመናችሁት ይህንኑ ነው። ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ፥ ከእናንተ አንዳንዶቹ እንዴት የሙታን ትንሣኤ የለም ይላሉ? የሙታን ትንሣኤ ከሌለማ ክርስቶስም አልተነሣም ማለት ነው። ክርስቶስም ካልተነሣ ስብከታችን ዋጋ ቢስ ነው፤ እምነታችሁም ከንቱ ነው። ደግሞም እግዚአብሔር ክርስቶስን ከሞት አስነሥቶታል ብለን በመመስከራችን፥ ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን የማይነሡ ከሆነ፥ ክርስቶስንም አላስነሣውም ማለት ነው፤ ምክንያቱም ሙታን ካልተነሡ፥ ክርስቶስም አልተነሣም። ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም እስከ አሁን ድረስ ከነኀጢአታችሁ አላችሁ ማለት ነው። በክርስቶስም ያንቀላፉት ጠፍተዋል ማለት ነው። ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለዚህች ሕይወት ብቻ ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን። ነገር ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵራት ሆኖ በእርግጥ ከሙታን ተነሥቶአል።