1 ቆሮንቶስ 14:4-6
1 ቆሮንቶስ 14:4-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ያንጻል። ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወድዳለሁ፤ ከዚህ ይልቅ ግን ትንቢትን ብትናገሩ እወድዳለሁ። ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ በልሳን የሚናገር ሰው የተናገረውን ካልተረጐመ፣ በልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ፣ በመግለጥ ወይም በዕውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኋችሁ በልሳን ብናገር ምን እጠቅማችኋለሁ?
1 ቆሮንቶስ 14:4-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ሰው ራሱን ብቻ ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበረ ክርስቲያንን ያንጻል። ሁላችሁም በተለያዩ ቋንቋዎች ብትናገሩ እወድ ነበር፤ ይበልጥ የምወደው ግን ትንቢትን ብትናገሩ ነው፤ ማኅበረ ምእመናን እንዲታነጽ በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የሚተረጒም ከሌለ፥ በተለያዩ ቋንቋዎች ከሚናገር ሰው ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ሰው ይበልጣል። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተናገርኩ ብመጣ ምን እጠቅማችኋለሁ? ይልቅስ የምጠቅማችሁ የእግዚአብሔርን ምሥጢር መግለጥን፥ ዕውቀትን፥ ትንቢት መናገርን፥ ትምህርትን ይዤላችሁ ብመጣ ነው።
1 ቆሮንቶስ 14:4-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በቋንቋ የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ የሚተረጕም ግን የክርስቲያን ማኅበርን ያንጻል። ሁላችሁም በቋንቋ ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ይልቁንም ትንቢት ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ሳይተረጕም በቋንቋ ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር እጅግ ይበልጣልና፤ ቢተረጕም ግን ማኅበሩን ያንጻል። አሁንም ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በማታውቁት ቋንቋ ባነጋግራችሁ፥ የጥበብ ነገርንም ቢሆን፥ የትንቢትንም ነገር ቢሆን፥ የማስተማር ሥራንም ቢሆን ገልጬ ካልነገርኋችሁ የምጠቅማችሁ ጥቅም ምንድን ነው?
1 ቆሮንቶስ 14:4-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ያንጻል። ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወድዳለሁ፤ ከዚህ ይልቅ ግን ትንቢትን ብትናገሩ እወድዳለሁ። ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ በልሳን የሚናገር ሰው የተናገረውን ካልተረጐመ፣ በልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ፣ በመግለጥ ወይም በዕውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኋችሁ በልሳን ብናገር ምን እጠቅማችኋለሁ?
1 ቆሮንቶስ 14:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል። ሁላችሁ በልሳኖች ልትናገሩ እወድ ነበር፥ ትንቢትን ልትናገሩ ግን ከዚህ ይልቅ እወዳለሁ፤ ማኅበሩ ይታነጽ ዘንድ ንግግሩን ባይተረጐም በልሳኖች ከሚናገር ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል። አሁን ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በልሳኖች ብናገር፥ በመግለጥ ወይም በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኋችሁ ምን እጠቅማችኋለሁ?
1 ቆሮንቶስ 14:4-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ሰው ራሱን ብቻ ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበረ ክርስቲያንን ያንጻል። ሁላችሁም በተለያዩ ቋንቋዎች ብትናገሩ እወድ ነበር፤ ይበልጥ የምወደው ግን ትንቢትን ብትናገሩ ነው፤ ማኅበረ ምእመናን እንዲታነጽ በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የሚተረጒም ከሌለ፥ በተለያዩ ቋንቋዎች ከሚናገር ሰው ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ሰው ይበልጣል። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተናገርኩ ብመጣ ምን እጠቅማችኋለሁ? ይልቅስ የምጠቅማችሁ የእግዚአብሔርን ምሥጢር መግለጥን፥ ዕውቀትን፥ ትንቢት መናገርን፥ ትምህርትን ይዤላችሁ ብመጣ ነው።
1 ቆሮንቶስ 14:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ያንጻል። ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወዳለሁ፤ ከዚህ ይልቅ ግን ትንቢትን ብትናገሩ እወዳለሁ። ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ በልሳን የሚናገር ሰው የተናገረውን ካልተረጐመ፥ በልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በልሳኖች ብናገር፥ በመግለጥ፥ በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኩአችሁ ምን እጠቅማችሃለሁ?