የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 14

14
በቋ​ንቋ ስለ መና​ገ​ርና ስለ መተ​ር​ጐም ሀብት
1ፍቅ​ርን ተከ​ተ​ሏት፤ ለመ​ን​ፈ​ሳዊ ስጦታ፥ ይል​ቁ​ንም ትን​ቢት ለመ​ና​ገር ተፎ​ካ​ከሩ። 2በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ ለሰው የሚ​ና​ገር አይ​ደ​ለም። የሚ​ና​ገ​ረ​ውን የሚ​ሰ​ማው የለ​ምና፥ ነገር ግን በመ​ን​ፈስ ምሥ​ጢ​ርን ይና​ገ​ራል። 3ትን​ቢ​ትን የሚ​ና​ገር ግን ለማ​ነ​ጽና ለመ​ም​ከር፥ ለማ​ረ​ጋ​ጋ​ትም ለሰው ይና​ገ​ራል። 4በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ራሱን ያን​ጻል፤ የሚ​ተ​ረ​ጕም ግን የክ​ር​ስ​ቲ​ያን ማኅ​በ​ርን ያን​ጻል። 5ሁላ​ች​ሁም በቋ​ንቋ ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ትን​ቢት ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ሳይ​ተ​ረ​ጕም በቋ​ንቋ ከሚ​ና​ገር ይልቅ ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እጅግ ይበ​ል​ጣ​ልና፤ ቢተ​ረ​ጕም ግን ማኅ​በ​ሩን ያን​ጻል።
6አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ወደ እና​ንተ መጥቼ በማ​ታ​ው​ቁት ቋንቋ ባነ​ጋ​ግ​ራ​ችሁ፥ የጥ​በብ ነገ​ር​ንም ቢሆን፥ የት​ን​ቢ​ት​ንም ነገር ቢሆን፥ የማ​ስ​ተ​ማር ሥራ​ንም ቢሆን ገልጬ ካል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የም​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ጥቅም ምን​ድን ነው? 7ነፍስ የሌ​ለው ድምፅ የሚ​ሰጥ እንደ መሰ​ንቆ፥#ግሪኩ “እንደ ዋሽ​ንት” ይላል። ወይም እንደ ክራር ያለ መሣ​ሪያ በስ​ልት ካል​ተ​መታ መሰ​ን​ቆው ወይም ክራሩ የሚ​ለ​ውን ማን ያው​ቃል? 8መለ​ከት የሚ​ነ​ፋም በታ​ወ​ቀው ስልት ካል​ነፋ ለጦ​ር​ነት ማን ይዘ​ጋ​ጃል? 9እን​ዲ​ሁም እና​ንተ በማ​ይ​ታ​ወቅ ቋንቋ ብት​ና​ገሩ፥ ይህ​ን​ኑም ገል​ጣ​ችሁ ባት​ተ​ረ​ጕሙ የም​ት​ሉ​ት​ንና የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን ማን ያው​ቃል? ከነ​ፋስ ጋር እን​ደ​ም​ት​ነ​ጋ​ገሩ ትሆ​ና​ላ​ችሁ። 10በዓ​ለም ልዩ ልዩ ቋን​ቋ​ዎች አሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ትር​ጕም የሌ​ለው አን​ድም የለም። 11የቋ​ን​ቋ​ውን ትር​ጓሜ ካላ​ወ​ቅሁ እኔ ለሚ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ረኝ እንደ እን​ግዳ እሆ​ን​በ​ታ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ረኝ እር​ሱም ለእኔ እንደ እን​ግዳ ይሆ​ናል። 12እን​ዲሁ እና​ን​ተም ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ ስጦታ ተፎ​ካ​ከሩ፤ ትበ​ዙም ዘንድ ማኅ​በሩ የሚ​ታ​ነ​ጽ​በ​ትን ፈልጉ። 13በማ​ያ​ው​ቀው ቋንቋ የሚ​ና​ገር ሰውም መተ​ር​ጐም እን​ዲ​ችል ይጸ​ልይ። 14በማ​ላ​ው​ቀው ቋንቋ የም​ጸ​ልይ ከሆ​ንሁ ቃሌ ብቻ ይጸ​ል​ያል፤ ልቤ ግን ባዶ ነው። 15እን​ግ​ዲህ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ በመ​ን​ፈስ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እማ​ል​ዳ​ለሁ፤ በመ​ን​ፈሴ እዘ​ም​ራ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እዘ​ም​ራ​ለሁ። 16አንተ በመ​ን​ፈስ ብታ​መ​ሰ​ግን፥ ያ የቆ​መው ያል​ተ​ማ​ረው በአ​ንተ ምስ​ጋና ላይ እን​ዴት አሜን ይላል? የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና የም​ት​ጸ​ል​የ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና። 17እነሆ፥ አን​ተስ መል​ካም ታመ​ሰ​ግ​ና​ለህ፤ ነገር ግን ሌላው እን​ዴት ይታ​ነ​ጻል? 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤ ከሁ​ላ​ችሁ ይልቅ እኔ በቋ​ን​ቋ​ዎች እና​ገ​ራ​ለ​ሁና። 19ነገር ግን ሌሎ​ችን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በቋ​ንቋ ከሚ​ነ​ገር ብዙ ቃል ይልቅ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በአ​እ​ም​ሮዬ አም​ስት ቃላ​ትን ልና​ገር እሻ​ለሁ።
20ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በአ​እ​ምሮ እንደ ሕፃ​ናት አት​ሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃ​ናት ሁኑ፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ፍጹ​ማን ሁኑ። 21#ኢሳ. 28፥11-12። በኦ​ሪ​ትም፥ “ይህን ሕዝብ በሌ​ሎች ቋን​ቋ​ዎ​ችና በሌላ አን​ደ​በት እና​ገ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዲ​ሁም ሆኖ አይ​ሰ​ሙ​ኝም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ​አል። 22አሁ​ንም ቋንቋ መና​ገር ለማ​ያ​ምኑ ሰዎች ለም​ል​ክት ነው፤ ለሚ​ያ​ምኑ ግን አይ​ደ​ለም፤ ትን​ቢ​ትም ለሚ​ያ​ምኑ ነው እንጂ ለማ​ያ​ምኑ አይ​ደ​ለም። 23ሕዝቡ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ቢሰ​በ​ሰቡ፥ ሁሉም በልዩ ልዩ ቋንቋ ቢና​ገሩ፥ አላ​ዋ​ቂ​ዎች፥ ወይም የማ​ያ​ምኑ ቢመጡ አብ​ደ​ዋል ይሉ​አ​ቸው የለ​ምን? 24ሁሉም ትን​ቢት ቢና​ገሩ ግን የማ​ያ​ምኑ ወይም አላ​ዋ​ቂ​ዎች ቢመጡ ሁሉ ይከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው የለ​ምን? ሁሉስ ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ቸው የለ​ምን? 25በል​ባ​ቸው የደ​በ​ቁ​ትም ይገ​ለ​ጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማ​ያ​ም​ነው ተመ​ልሶ ይጸ​ጸ​ታል፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ግ​ዳል፥ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳ​ለም ይና​ገ​ራል።
ስለ ጸሎተ ማኅ​በር ሥር​ዐት
26አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ሁላ​ችሁ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ መዝ​ሙር አላ​ችሁ፤ ትም​ህ​ርት አላ​ችሁ፤ መግ​ለጥ አላ​ችሁ፤ በቋ​ንቋ መና​ገር አላ​ችሁ፤ መተ​ር​ጐ​ምም አላ​ችሁ፤ ሁሉም ለሚ​ታ​ነ​ጽ​በት ጥቅም አድ​ር​ጉት። 27በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ቢኖር ሁለት ሁለት፥ ወይም ቢበዛ ሦስት ሦስት እየ​ሆኑ በተራ ይና​ገሩ፤ ሌላ​ውም ይተ​ር​ጕ​ም​ለት። 28የሚ​ተ​ረ​ጕም ከሌለ ግን በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገ​ረው ዝም ይበል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መካ​ከ​ልና በእ​ርሱ መካ​ከል ይና​ገር። 29ነቢ​ያ​ትም ቃላ​ቸው ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ይታ​ወቅ ዘንድ ሁለት ሁለት፥ ወይም ሦስት ሦስት ሆነው ይና​ገሩ። 30ተቀ​ምጦ ሳለ ምሥ​ጢር የተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ቢኖር ፊተ​ኛው ዝም ይበል። 31ሁሉ እን​ዲ​ማር፥ ሁሉም ደስ እን​ዲ​ለው፥ እን​ዲ​ጸ​ናም ሁላ​ችሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ትን​ቢት ልት​ና​ገሩ ትች​ላ​ላ​ች​ሁና። 32የነ​ቢ​ያት ሀብት ለነ​ቢ​ያት ይሰ​ጣ​ልና። 33በቅ​ዱ​ሳን ጉባኤ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ደ​ረግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ላም አም​ላክ እንጂ የሁ​ከት አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ምና። 34ሴቶ​ችም በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ዝም ይበሉ፤ ሊታ​ዘዙ እንጂ ሊና​ገሩ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ምና፤ ኦሪ​ትም እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና። 35ለሴት በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን መና​ገር ክል​ክል ነው፤ ሊማሩ ከወ​ደዱ ደግሞ በቤ​ታ​ቸው ባሎ​ቻ​ቸ​ውን ይጠ​ይቁ። 36የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከእ​ና​ንተ ብቻ ወጥ​ቶ​አ​ልን? ወይስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እና​ንተ ብቻ ደር​ሶ​አ​ልን?
37ራሱን እንደ ነቢይ አድ​ርጎ ወይም መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዳ​ደ​ረ​በት አድ​ርጎ የሚ​ቈ​ጥር ቢኖር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ነውና ይህን የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ች​ሁን ይወቅ። 38ነገር ግን ይህን የማ​ያ​ውቅ ቢኖር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አያ​ው​ቀ​ውም። 39አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ትን​ቢ​ትን ለመ​ና​ገር ቅኑ፤ በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አት​ከ​ል​ክ​ሉት። 40ነገር ግን ሁሉን በአ​ገ​ባ​ብና በሥ​ር​ዐት አድ​ርጉ፤

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ