1 ቆሮንቶስ 1:4-6
1 ቆሮንቶስ 1:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ፤ ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፥ በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና።
1 ቆሮንቶስ 1:4-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ተሰጣችሁ ጸጋ ስለ እናንተ አምላኬን ሁልጊዜ አመሰግናለሁ። ምክንያቱም በማናቸውም ነገር ይኸውም በንግግር ሁሉ፣ በዕውቀትም ሁሉ በርሱ በልጽጋችኋል፤ ስለ ክርስቶስ የመሰከርንላችሁም በእናንተ ዘንድ ጸንቷል።
1 ቆሮንቶስ 1:4-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ስለ እናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ ስለተሰጣችሁ ጸጋ ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። በአነጋገር ሁሉ፥ በዕውቀትም ሁሉ ከብራችሁበታልና። ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ እንደ ጸና መጠን።