ትንቢተ ዘካርያስ 7:9-10

ትንቢተ ዘካርያስ 7:9-10 አማ54

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፥ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፥ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፥ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ።