የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዘካርያስ 3

3
1እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም ይከስሰው ዘንድ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር። 2እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ሰይጣን ሆይ፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፥ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፥ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን? አለው። 3-4ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር። እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው። እርሱንም፦ እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ አለው። 5ደግሞ፦ ንጹሕ ጥምጥም በራስ ላይ አድርጉ አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፥ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።
6የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያሱ እንዲህ ሲል አዳኘበት፦ 7የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ። 8ታላቁ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ፥ በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮች ለምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፥ እነሆ፥ እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ። 9በኢያሱ ፊት ያኖርሁት ድንጋይ እነሆ አለ፥ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፥ እነሆ፥ ቅርጹን እቀርጻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ። 10በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ሆኖ ባልንጀራውን ይጠራል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ