በምሳም ጊዜ ቦዔዝ “ወደዚህ ቅረቢ፤ ምሳ በዪ፤ እንጀራሽንም በሆምጣጤው አጥቅሽ፤” አላት። በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች፤ የተጠበሰም እሸት ሰጣት፤ በልታም ጠገበች፤ አተረፈችም። ደግሞም ልትቃርም በተነሣች ጊዜ ቦዔዝ ጐበዛዝቱን “በነዶው መካከል ትቃርም፤ እናንተም አታሳፍሩአት፤ ደግሞ ከነዶው አስቀርታችሁ ተዉላት፤ እርስዋም ትቃርም፤ አትውቀሱአትም፤” ብሎ አዘዛቸው። በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፤ የቃረመችውንም ወቃችው፤ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህልም ገብስ ሆነ። ተሸክማውም ወደ ከተማ ገባች፤ አማትዋም የቃረመችውን አየች፤ ከጠገበችም በኋላ የተረፋትን አውጥታ ሰጠቻት። አማትዋም “ዛሬ ወዴት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን፤” አለቻት። እርስዋም “ዛሬ የሠራሁበት ሰው ስም ቦዔዝ ይባላል፤” ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማትዋ ነገረቻት። ኑኃሚንም ምራትዋን “ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን፤” አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ “ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፤ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው፤” አለቻት። ሞዓባዊቱ ሩትም “ደግሞ ‘መከሬን እስኪጨርሱ ድረስ ጐበዛዝቴን ተጠጊ፤’ አለኝ፤” አለቻት። ሚኃሚንም ምራትዋን ሩትን “ልጄ ሆይ! ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው፤” አለቻት። ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝን ገረዶች ተጠጋች፤ በአማትዋም ዘንድ ትቀመጥ ነበር።
መጽሐፈ ሩት 2 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ሩት 2:14-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos