የሉቃስ ወንጌል 22:1-6

የሉቃስ ወንጌል 22:1-6 አማ54

ፋሲካም የሚባለው የቂጣ በዓል ቀረበ። የካህናት አለቆችና ጻፎችም እንዴት እንዲያጠፉት ይፈልጉ ነበር፤ ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና። ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ፤ ሄዶም እንዴት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከመቅደስ አዛዦች ጋር ተነጋገረ። እነርሱም ደስ አላቸው፥ ገንዘብም ሊሰጡት ተዋዋሉ። እሺም አለ፥ ሕዝብም በሌለበት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።