ሰቈቃወ ኤርምያስ 3:19-33

ሰቈቃወ ኤርምያስ 3:19-33 አማ54

ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ። ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች። ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ። ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፥ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ነፍሴ፦ እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፥ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች። ጤት። እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው። ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው። ሰው በታናሽነቱ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው። ዮድ። እርሱ አሸክሞታልና ዝም ብሎ ለብቻው ይቀመጥ። ተስፋ የሆነው እንደ ሆነ አፉን በአፈር ውስጥ ያኑር። ጕንጩን ለሚመታው ይስጥ፥ ስድብንም ይጥገብ። ካፍ። ጌታ ለዘላለም አይጥልምና፥ ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራልና፥ የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅም፥ አያሳዝንምም።