የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢያሱ 19

19
1ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፥ ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መከከል ነበረ። 2እነዚህም ርስታቸው ሆኑላቸው፥ ቤርሳቤህ፥ ሤባ፥ ሞላዳ፥ 3-4ሐጸርሹዓል፥ ባላ፥ ዔጼም፥ ኤልቶላድ፥ 5በቱል፥ ሔርማ፥ ጺቅላግ፥ ቤትማርካቦት፥ 6ሐጸርሱሳ፥ ቤተ ለባኦት፥ ሻሩሔን፥ አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው፥ 7ዓይን፥ ሪሞን፥ ዔቴር፥ አሻን፥ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው፥ 8እስከ ባዕላትብኤርና እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። 9ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፥ የይሁዳም ልጆች እድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ።
10ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ፥ የርስታቸውም ድንበር ወደ ሣሪድ ደረሰ፥ 11ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼትም ደረሰ፥ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ፥ 12ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎትታቦር ዳርቻ ዞረ፥ 13ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ፥ ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒታቃጺን አለፈ፥ ወደ ሪምንና ወደ ኒዓ ወጣ። 14ድንበሩም በሰሜን በኩል ወደ ሐናቶን ዞረ፥ መውጫውም በይፍታሕኤል ሸለቆ ነበረ። 15ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም፥ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 16የዛብሎን ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
17አራተኛውም ዕጣ ለይሳኮር ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። 18ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥ 19ወደ ከስሎት፥ ወደ ሱነም፥ ወደ ሐፍራይም፥ ወደ ሺኦን፥ ወደ አናሐራት፥ 20ወደ ረቢት፥ ወደ ቂሶን፥ ወደ አቤጽ፥ 21ወደ ሬሜት፥ ወደ ዓይንጋኒም፥ ወደ ዓይንሐዳ፥ ወደ ቤትጳጼጽ ደረሰ፥ 22ድንበሩም ወደ ታቦርና ወደ ሻሕጹማ፥ ወደ ቤትሳሚስ ደረሰ፥ የድንበራቸውም መውጫ ዮርዳኖስ ነበረ፥ አሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 23የይሳኮር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
24አምስተኛውም ዕጣ ለአሴር ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። 25ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥ ቤጤን፥ አዚፍ፥ 26አላሜሌክ፥ ዓምዓድ፥ ሚሽአል ነበረ፥ በምዕራብ በኩል ወደ ቀርሜሎስና ወደ ሺሖርሊብናት ደረሰ፥ 27ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤትዳጎን ዞረ፥ ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፥ በስተ ግራ በኩልም ወደ ካቡል ወጣ፥ 28ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲዶናም ደረሰ። 29ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፥ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፥ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፥ 30ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ፥ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 31የአሴር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
32ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። 33ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ ከጸዕነኒም ዛፍ፥ ከአዳሚኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፥ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ። 34ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፥ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ። 35የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ነበሩ፥ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ 36ረቃት፥ ኬኔሬት፥ አዳማ፥ ራማ፥ አሶር፥ 37-38ቃዴስ፥ ኤድራይ፥ ዓይንሐጾር፥ ይርኦን፥ ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤትዓናት፥ ቤትሳሚስ፥ አሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። 39የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
40ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። 41የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ፥ ጾርዓ፥ ኤሽታኦል፥ ዒርሼሜሽ፥ 42-43ሸዕለቢን፥ ኤሎን፥ ይትላ፥ ኤሎን፥ ትምና፥ 44አቃሮን፥ ኢልተቄ፥ ገባቶን፥ ባዕላት፥ 45-46ይሁድ፥ ብኔብረቅ፥ ጋትሪሞን፥ ሜያርቆን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆን። 47የዳንም ልጆች ዳርቻ አልበቃቸውም፥ የዳንም ልጆች ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም፥ ስምዋንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት። 48የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
49ምድሩንም ሁሉ በየድንበሩ ርስት እንዲሆን ከፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት። 50በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት፥ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት።
51ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም መካፈል ጨረሱ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ