መጽሐፈ ኢዮብ 8
8
1ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦
2እስከ መቼ ይህን ትናገራለህ?
የአፍህስ ቃል እስከ መቼ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናል?
3በውኑ እግዚአብሔር ፍርድን ያጣምማልን?
ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?
4ልጆችህ በድለውት እንደ ሆነ፥
እርሱ በበደላቸው እጅ ጥሎአቸዋል።
5እግዚአብሔርን ብትገሠግሥ፥
ሁሉንም የሚችለውን አምላክ ብትለምን፥
6ንጹሕና ቅን ብትሆን፥
በእውነት አሁን ስለ አንተ ይነቃል፥
የጽድቅህንም መኖሪያ ያከናውንልሃል።
7ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳ
ፍጻሜህ እጅግ ይበዛል።
8-9ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነውና
እኛ የትናንት ብቻ ነን፥ ምንም አናውቅም፥
ስለዚህ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፥
አባቶቻቸውም ለመረመሩት ነገር ትጋ፥
10እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥
ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?
11በውኑ ደንገል ረግረግ በሌለበት መሬት ይበቅላልን?
ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?
12ገና ሲለመልም ሳይቈረጥም፥
ከአትክልት ሁሉ በፊት ይደርቃል።
13እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፥
የዝንጉም ሰው ተስፋ ይጠፋል።
14ተስፋው ይቈረጣል፥
እምነቱም እንደ ሸረሪት ቤት ይሆናል።
15ቤቱን ይደግፈዋል፥ አይቆምለትም፥
ይይዘውማል፥ አይጸናለትም።
16ፀሐይም ሳይተኵስ ይለመልማል፥
ጫፉም በአታክልቱ ቦታ ይወጣል።
17በድንጋይ ክምር ላይ ሥሩ ይጠመጠማል፥
የድንጋዩቹን ቦታ ይመለከታል።
18ከቦታው ቢጠፋ፦
አላየሁህም ብሎ ይክደዋል።
19እነሆ፥ የመንገዱ ደስታ እንዲህ ነው፥
ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ።
20እነሆ፥ እግዚአብሔር ፍጹሙን ሰው አይጥለውም፥
የኃጢአተኞችንም እጅ አያበረታም።
21አፍህን እንደ ገና ሳቅ ይሞላል፥
ከንፈሮችህንም እልልታ ይሞላል።
22የሚጠሉህ እፍረት ይለብሳሉ፥
የኃጢአተኞችም ድንኳን አይገኝም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 8: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ