የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 31:1-12

መጽሐፈ ኢዮብ 31:1-12 አማ54

ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ እንግዲህስ ቈንጆይቱን እንዴት እመለከታለሁ? የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ከላይ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ርስት ከአርያም ምንድር ነው? መዓትስ ለኃጢአተኛ፥ መለየትስ ለሚበድሉ አይደለችምን? መንገዴን አያይምን? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን? በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ቅንነቴን ይወቅ። በሐሰት ሄጄ እንደ ሆነ እግሬም ለሽንገላ ቸኵላ እንደ ሆነ፥ እርምጃዬ ከመንገድ ፈቀቅ ብሎ፥ ልቤም ዓይኔን ተከትሎ፥ ነውርም ከእጄ ጋር ተጣብቆ እንደ ሆነ፥ እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብላው፥ የሚበቅለውም ሁሉ ይነቀል። ልቤ ወደ ሌላይቱ ሴት ጐምጅቶ እንደ ሆነ፥ በባልንጀራዬም ደጅ አድብቼ እንደ ሆነ፥ ሚስቴ ለሌላ ሰው ትፍጭ፥ ሌሎችም በእርስዋ ላይ ይጐንበሱ። ይህ ክፉ አበሳ፥ ፈራጆችም የሚቀጡበት በደል ነውና፥ ይህ እስከ ጥፋት ድረስ የሚበላ እሳት፥ ቡቃያዬንም ሁሉ የሚነቅል ነውና።