የዮሐንስ ወንጌል 7:3-5

የዮሐንስ ወንጌል 7:3-5 አማ54

እንግዲህ ወንድሞቹ፦ “ደቀ መዛሙርትህ ደግሞ የምታደርገውን ሥራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሣና ወደ ይሁዳ ሂድ፤ ራሱ ሊገልጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ብታደርግ ራስህን ለዓለም ግለጥ” አሉት። ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና።