የዮሐንስ ወንጌል 6:32-35

የዮሐንስ ወንጌል 6:32-35 አማ54

ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና አላቸው። ስለዚህ፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፥ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።