የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮሐንስ ወንጌል 19:14-16

የዮሐንስ ወንጌል 19:14-16 አማ54

ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ ስድስት ሰዓትም የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም፦ “እነሆ ንጉሣችሁ” አላቸው። እነርሱ ግን፦ “አስወግደው፥ አስወግደው፥ ስቀለው” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም፦ “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አላቸው። የካህናት አለቆችም፦ “ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ብለው መለሱለት ስለዚህ በዚህን ጊዜ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው።