የዮሐንስ ወንጌል 14:4-6

የዮሐንስ ወንጌል 14:4-6 አማ54

ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ።” ቶማስም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው። ኢየሱስም፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።