ትንቢተ ኤርምያስ 28:15-16

ትንቢተ ኤርምያስ 28:15-16 አማ54

ነቢዩም ኤርምያስ ነቢዩን ሐናንያን፦ ሐናንያ ሆይ፥ ስማ፥ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ እግዚአብሔር አልላከህም። ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከምድር ላይ እሰድድሃለሁ፥ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ አለው።