የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ኢሳይያስ 9:2-7

ትንቢተ ኢሳይያስ 9:2-7 አማ54

በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፥ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው። ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፥ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል። በምድያም ጊዜ እንደሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር ያስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል። የሚረግጡ የሠልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል። ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፥ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፥ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።