የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ታምሞ ከደዌው በተፈወሰ ጊዜ የጻፈው ጽሕፈት ይህ ነው፦ እኔ፦ በሕይወት ዘመኔ መካከል ወደ ሲኦል በሮች እገባለሁ፥ የቀረው ዘመኔ ጐደለብኝ አልሁ። ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር እግዚአብሔርን አላይም፥ በዓለምም ከሚኖሩ ጋር ሰውን እንግዲህ አልመለከትም አልሁ። ማደሪያዬ ተነቀለች፥ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፥ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፥ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ። እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፥ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ። እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፥ ዓይኖቼ ወደ ላይ ከማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ። ምን እላለሁ? እርሱ ተናግሮኛል፥ እርሱ ራሱም ይህን አድርጎአል፥ በዘመኔ ሁሉ ስለ ነፍሴ ምሬት ቀስ ብዬ እሄዳለሁ። ጌታ ሆይ፥ በዚህ ነገር ሰዎች በሕይወት ይኖራሉ፥ በዚህም ሁሉ የመንፈሴ ሕይወት ነው፥ አንተም ፈወስኸኝ ወደ ሕይወትም መለስኸኝ። እነሆ፥ ታላቅ ምሬት ለደኅንነቴ ሆነ፥ አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጕድጓድ አዳንሃት፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጣልህ። ሲኦል አያመሰግንህምና፥ ሞትም አያከብርህምና፥ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም። እኔ ዛሬ እንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፥ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል። እግዚአብሔር ያድነኛል፥ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው ዕቃ እንዘምራለን።
ትንቢተ ኢሳይያስ 38 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ኢሳይያስ 38:9-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች