ኦሪት ዘፍጥረት 8:15-20

ኦሪት ዘፍጥረት 8:15-20 አማ54

እግዚአብሔርም ለኖኅ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ አንተ ሚስትህንና ልጆችህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ከመርከብ ውጣ። ከአንተ ጋር ያሉትን አራዊት ሁሉ ሥጋ ያላቸውን ሁሉ፥ ወፎችንና እንስሶችን ሁሉ፥ ከአንተ ጋር አውጣቸው በምድር ላይ ይብዙ። ኖኅም ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወጣ። አራዊት ሁሉ፥ ተቀሳቃሾች ሁሉ፥ ወፎችም ሁሉ በምድር ላይ የሚርመሰምስው ሁሉ በየዘመዳቸው ከመርከብ ወጡ። ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጽሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችን ሁሉ ወሰደ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀርበ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}