የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 8:13-22

ኦሪት ዘፍጥረት 8:13-22 አማ54

በኖኅ ዕድሜ በስድስት መቶ አንድ ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ክዳን አነሣ፥ እነሆም ውኃው ከምድር ፊት እንደ ደረቀ አየ። በሁለተኛውም ወር ከወሩም በሀያ ሰባተኛውም ወር ቀን ምድር ደረቀች። እግዚአብሔርም ለኖኅ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ አንተ ሚስትህንና ልጆችህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ከመርከብ ውጣ። ከአንተ ጋር ያሉትን አራዊት ሁሉ ሥጋ ያላቸውን ሁሉ፥ ወፎችንና እንስሶችን ሁሉ፥ ከአንተ ጋር አውጣቸው በምድር ላይ ይብዙ። ኖኅም ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወጣ። አራዊት ሁሉ፥ ተቀሳቃሾች ሁሉ፥ ወፎችም ሁሉ በምድር ላይ የሚርመሰምስው ሁሉ በየዘመዳቸው ከመርከብ ወጡ። ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጽሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችን ሁሉ ወሰደ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀርበ። እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ ምድርን ዳግመኛ ስለ ስው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉት እንደ ገና አልመታም። በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}