ኦሪት ዘፍጥረት 7:17-24

ኦሪት ዘፍጥረት 7:17-24 አማ54

የጥፋትም ውኂ በምድር ላይ አርባ ቀን ነበረ ውኂውም በዛ መርከቢቱንም አነሣ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች። ውኂውም አሸነፈ፤ በምድር ላይም እጅግ በዛ መርከቢቱም በውኂ ላይ ሄደች። ውኂውም በምድር ላይ እጅግ በጣም አሽነፈ ከሰማይም በታች ያሉ ታላላቆች ተራሮች ሁሉ ተሸፈኑ። ውኂው ወደ ላይ አሥራ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ ተራሮችም ተሸፈኑ። በምድር ላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቃሹም ሁሉ ሰውም ሁሉ ጠፉ። በየብስ የነበረው በአፍንጫው የሕይወት ነፍስ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሞተ። በምድር ላይ የነበውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ፤ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፤ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ ተደመሰሰ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ። ውኅውም መቶ አምሳ ቀን በምድር ላይ አሸነፈ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}