የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 6:17-22

ኦሪት ዘፍጥረት 6:17-22 አማ54

እኔም እነሆ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኂን አመጣለሁ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል። ቃል ኪዳኔም ከአንተ ጋር አቆማለሁ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ። ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለር እያደረግህ ወደ መርከብ ታገባለህ ተባትና እንስት ይሁን። ከወፍ እንደ ወገኑ ከእንስሳም እንደ ወገኑ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንድ ወገኑ በሕይውር ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆን ወደ አንተ ይግቡ። ከሚበላውም መብል ሁሉ ለአንተ ውሰድ፤ ወደ አንተም ትሰበስባለህ እርሱም ለአንተም ለእነርሱም መብል ይሆናል። ኖኅም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}