የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 50:15-21

ኦሪት ዘፍጥረት 50:15-21 አማ54

የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዪ ጊዜ እንዲህ አሉ፦ ምናልባትም ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል ባደረግንበትን ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል። ወደ ዮሴፍም መልእክት ላኩ እንዲህም አሉት፦ አባትህ ገና ሳይሞት እንዲህ ብሎ አዝዞአል፦ ዮሴፍን እንዲህ በሉት፦ እባክህ የውንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና አሁን እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉን ይቅር በል። ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው፦ እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን አሉት። ዮሴፍም አላቸው፦ አትፍሩ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን? እናንተ ክፋ ነገርን አሰባችሁብኝ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው። አሁንም አትፍሩ እኔ እናንተና ልጆቻችሁን እመግባችኍለሁ አጽናናቸውም ደስ አሰኛቸውም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}