የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 5:1-32

ኦሪት ዘፍጥረት 5:1-32 አማ54

የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው። አዳምም ሴትን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወስደ። አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ሞተም። ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፤ ሄኖስንም ወለደ፤ ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ሴትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥራ ሁለት ዓመት ሆነ ሞተም። ሄኖስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ፤ ቃይናንንም ወለደ፤ ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ አሥራ አምስት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ሄኖስም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ ሞተም። ቃይናንም መቶ ሰባ ዓምት ኖረ፤ መላልኤልንም ወለደ፤ ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ አርባ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥር ዓመት ሆነ ሞተም። መላልኤልም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ያሬድንም ወለደ። መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንችም ወለደ። መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ ሞተም። ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሄኖክንም ወለደ ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኍላ የኖረው ስምንት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ ሞተም። ሄኖክም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ማቱሳላንም ወለደ፤ ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፤ ማቱሳላንም ከወለደ በኍላ የኖረው ሁለት መቶ ዓመት ሆነ ወለደ። ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ። ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና። ማቱሳላም መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ላሜሕንም ወለደ፤ ማቱሳላም ላሜሕን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ ሞትም። ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ልጅንም ወለደ። ስሙንም፤ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው። ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኍላ የኖረው አምስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ሆነ ሞተም። ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ፤ ኖኅም ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}