የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 49

49
1ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ በኍለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብስቡ። 2እናንት የያዕቆብ ልጆች ተሰብስቡ፥ ስሙም አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ። 3ሮቤል አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ የጕብዝናዬም መጀመሪያ ነህ፤ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ። 4እንደ ውኅ የምትዋልል ነህ አለቅነት ለአንተ አይሁን፤ ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና፤ አረከስኽውም ወደ አልጋዬም ወጣ። 5ስምዖንና ሌዊ ወንድማማች ናቸው ሰይፎቻቸው የዓመፅ መሣሪያ ናቸው። 6በምክራቸው ነፍሴ፥ አትግባ ከጉባኤአቸውም ጋር ክብሬ አትተባበር በቍጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክስዋልና። 7ቍጣቸው ርጉም ይሁን ጽኑ ነበርና ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ። 8ይሁዳ ወንድሞችህ አንተን ያመስግኑሃል እጅህ በጠላቶችህ ደንድስ ላይ ነው የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ። 9ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ ከአደንህ ወጣሁ እንደ አንበሳ አሸመቀ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፤ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል? 10በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል። 11ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል የአህያይቱንም ግልግል በወይን አረግ ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም። 12ዓይኑም ከወይን ይቀላል፤ ጥርሱም ከወተት ነጭ ይሆናል። 13ዛብሎን በባሕር ዳር ይቀመጣል እርሱም ለመርከቦች ወደብ ይሆናል ዳርቻውም እስከ ሲዶን ድረስ ነው። 14ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው በበጎች ጕረኖም መካከል ያርፋል 15ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን ትከሻውን ለመሸከም ዝቅ አደረገ በሥራም ገበሬ ሆነ። 16ዳም በወገኑ ይፈርዳል ከእስርኤል ነገስ እንደ አንዱ 17ዳን በጕዳና ላይ እንደ እባብ ይሆናል በመንገድም እንደ ቀንዳም እባብ ፈረሱን ከሰኮናው ይነክሳል ፈረስኛም ወደኍላው ይወድቃል። 18እግዚእብሔር ሆይ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ። 19ጋድም ዘማቾች ይዘምቱበታል እርሱ ግን ተከታትሎ ይዘምትባቸዋል 20የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይስጣል። 21ንፍታሌም የተፈታ ሚዳቋ ነው፤ መልካም ቃልን ይሰጣል። 22ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ። 23ቀስተኞች አስቸገሩት ነደፋትም ተቃወሙትም ነገር ግም ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፤ 24የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል ዓምድ 25በአባትህ በአምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ በጥልቅ በረከት ከታች በሚሠራጭ በጡትና በማኅፀን በረከት። 26የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኅያላን ናቸው፤ ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮርፍቶች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ። 27ብንያም ነጣቂ ተኵላ ነው፤ የበዘበዛውን በጥዋት ይበላል የማረከውንም በማታ ይካፈላል። 28እነዚህም ሁሉ አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው። 29እንዲህ ብሎም አዘዛቸው፦ እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ 30እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት። 31አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኍት፤ 32እርሻውና በእርስዋ ላይ ያለችው ዋሻ ከኬጢ ልጆች የተገዙ ናቸው። 33ያዕቆብ ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹ በአልጋው ላይ ሰብስቦ ሞተ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ