ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ። በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን ዓመታ እህል ሁሉ ሰበሰበ እህልንም በከተማቹ አደለበ፤ በየከተማይቱ ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ። ዮሴፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስንዴን አከማቸ መሰፈርን እስኪተው ድረስ ሊሰፈር አልተቻለምና። ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት። ዮሴፍም የበኵር ልጅን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረስኝ የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ። በግብፅ ምድር የነበረውም የሰባቱ ዓመት ጥጋብ አለፈ፥ ዮሴፍም እንደ ተናገረ የሰባቱ ዓመት ራብ ጀመረ። በየአገሩም ሁሉ ራብ ሆነ በግብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ። የግብፅ ምድርም ሁሉ ተራበ ሕዝቡም ስለ እህል ወደ ፈርዖን ጮኽ ፈርዖንም የግብፅ ሰዎችን ሁሉ፦ ወደ ዮሴፍ ሂዱ፥ እርሱ ያላችሁንም ሁሉ አድርጉ አላቸው። በምድርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ ዮሴፍም እህል ያለበትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ ራብም በግብፅ ምድር ጸንቶ ነበር። አገሮችም ሁሉ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወደ ዮሴፍ መጡ በምድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበርና።
ኦሪት ዘፍጥረት 41 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 41:47-57
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos