ዮሴፍም አለው፦ የዚህ ትርጓሜው ይህ ነው፤ ሦስት አረግ ሦስት ቀን ነው እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ከፍ ያደርጋል፥ ወደ ቀደመው ሹመትህም ይመልስሃል ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታድርግ እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሥርዓትም የፈርዓንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ። ነገር ግን በጎ ነገር በተደረግልህ ጊዜ እኔን አስበኝ ምሕረትንም አድርግልኝ የእኔንም ነገር ለፈርዖን ነግረህ ከዚህ ቤት አውጣኝ፤ እኔን ከዕብራውያን አገር ሰርቀው አምጥተውኛልና ከዚህም ደግሞ በግዞት ያኖሩኝ ዘንድ ምንም አላደረግሁም። የእንጀራ አበዛቹ አለቃም ሕልሙን በመልካም እንደ ተረጎመ ባየ ጊዜ ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ እኔም ደግሞ ሕልም አይቼ ነበር እነሆም ሦስት መሶብ ነጭ እንጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤ በላይኛውም መሶብ ፈርዖን ከሚበላው ከጋጋዎች ሥራ ሁሉ ነበረበት፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከመሶቡ ይበሉ ነበር። ዮሴፍም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዚህ ትርጓሜው ይህ ነው ሦስት መሶብ ሦስት ቀን ነው። እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ከፍ ያደርጋል፥ በእንጨትም ላይ ይስቅልሃል ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል። በሦስተኛውም ቀን ፈርዖን የተወለደበት ቀን ነበረ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ከፍ አደረገ። የጠጅ አሳለፊዎቹንም አለቃ ወደ ስፍራው መለሰው ጽዋውንም በፈርዖን እጅ ሰጠ። የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ ሰቀለው ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው። የጠጅ አሳላፊዎች አለቃ ግን ዮሴፍን አላሰበውም ረሳው እንጂ።
ኦሪት ዘፍጥረት 40 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 40:12-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች