ኦሪት ዘፍጥረት 39:20-23

ኦሪት ዘፍጥረት 39:20-23 አማ54

የዮሴፍም ጌታ ወሰደው የንጉሠ እስረኞችም ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደ ግዞት ቤት አገባው፤ ከዚያም በግዞት ነበረ። እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት በግዞት ቤቱም አለቃ በግዞት ያሉትን እስረኞች ሁሉ በዮሴፍ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው በዚያም የሚደረገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚያደርገው ነበረ። የግዞት ቤቱን አለቃ በእጁ ያለውን ነገር ከቶ አላሰበም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}