የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 33:4-11

ኦሪት ዘፍጥረት 33:4-11 አማ54

ዔሳውም ሊገናኘው ሮጠ አንገቱንም አቅፎ ሳመው ተላቀሱም። ዓይኑንም አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ እንዲህም አለ፦ እነዚህ ምኖችህ ናቸው? እርሱም፦ እግዚአብሔር ለእኔ ለባሪያህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው አለ። ሴቶች ባሪያዎችም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው ሰገዱ ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀረበው ሰገዱ ከዚይም በኍላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ። እርሱም፦ ያገኘሁት ይህ ሠራዊት ሁሉ ምንህ ነው? አለ። እርሱም፦ በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ነው አለ። ዔሳውም፦ ለእኔ ብዙ አለኝ ወንድሜ ሆይ የአንተ ለአንተ ይሁን አለ። ያዕቆብም አለ፦ እንደዚህ አይደለም ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ መንሻዬን ተቀበለኝ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና በቸርነትም ተቀብለኸኛልና። ይህችንም ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል እግዚአብሔር በቸርነት ስጥቶኛልና ለእኔም ብዙ አለኝና። እስኪቀበለውም ድረስ ዘበዘበው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}