ኦሪት ዘፍጥረት 3:14-21

ኦሪት ዘፍጥረት 3:14-21 አማ54

እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረገህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህም ትሄዳለህ፤ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ። በአንተና በሴቲቱ መካከል፤ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል አንተም ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ። ለሴቲቱም አለ፤ በፀነሰሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ገዥሽ ይሆናል። አዳምም አለው፤ የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፤ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። ወደ ወጣህብት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀርን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና። አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፤ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና። እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፤ አለበሳቸውም። ፕ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}