ኦሪት ዘፍጥረት 11:11-30

ኦሪት ዘፍጥረት 11:11-30 አማ54

ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኍላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ቃይንምንም ወለደ፤ አርፋክስድም ቃይንምንም ከወለደ በኍላ አራት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችም ወለደ፥ ሞተም። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶቸም ወለደ፤ ሞተም። ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኍላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ዔበርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ ፋሌቅንም ወለደ፤ ዔበርም ፋሌቅን ከወለደ በኍላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ፤ ራግውንም ከወለደ በኍላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችን፥ ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ፤ ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኍላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ፤ ናኮርንም ከወለደ በኍላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ታራንም ወለደ፤ ታራንም ከወለደ በኍላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ ወንዶችን ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ። የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራም አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፤ ሐራንም ሎጥን ወለደ። ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ። አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፤ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዩስካ አባት ነው። ሦራም መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}