እግዚአብሔርም አለ፤ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ። እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን ከዋክብትም ደግሞ አደረገ። እግዚአሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፤ በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አራተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፤ ዉኂ ሕያዉ ነፍስ ያላቸዉን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ። እግዚእብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን ውኂይቱ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚእብሔርም እንድህ ብሎ ባረካቸው፤ ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኂ ሙሉአት ውፎችም በምድር ላይ ይብዙ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ አምስተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታዉጣ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ አደረገ እንስሳዉንም እንደ ወገኑ የመሬት ተንቀሳቃሾችም እንደ ወገኑ አደረገ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 1:14-25
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች