የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን መጡ፤ “ለምን በባሪያዎችህ እንዲህ ታደርጋለህ? ገለባ አይሰጡንም፤ የጡቡንም ሥራ እንድንሠራ ያዝዙናል፤ እነሆም ባሪያዎችህን ይገርፉናል፤ ግድፈቱ ግን በአንተ ሕዝብ ላይ ነው” ብለው ጮሁ። እርሱ ግን፦ “ሰልችታችኋል፤ ሰልችታችኋል፤ ስለዚህም፦ ‘እንሂድ ለእግዚአብሔርም እንሠዋ’ ትላላችሁ። አሁንም ሂዱ፤ ሥሩ፤ ገለባ አይሰጡአችሁም፤ የጡቡን ቁጥር ግን ታመጣላችሁ፤” አላቸው። የእስራኤልም ልጆች አለቆች፦ “ዕለት ዕለት ከምትሰሩት ከጡቡ ቁጥር ምንም አታጕድሉ!” ባሉአቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ። ከፈርዖንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴንና አሮንን በፊታቸው ቆመው ተገናኙአቸው። እነርሱም፦ “በፈርዖንና በባሪያዎቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድሉንም ዘንድ ሰይፍን በእጃቸው ሰጥታችኋቸዋልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም፤” አሉአቸው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመለሰና፦ “ጌታ ሆይ! ስለ ምን ይህን ሕዝብ አስከፋህ? ስለ ምንስ ላክኸኝ? በስምህ እናገር ዘንድ ወደ ፈርዖን ከገባሁ ወዲህ ይህን ሕዝብ አስከፍቶታልና፤ አንተም ሕዝብህን ከቶ አላዳንኸውም፤” አለ።
ኦሪት ዘጸአት 5 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘጸአት 5:15-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች