የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘጸአት 4:1-13

ኦሪት ዘጸአት 4:1-13 አማ54

ሙሴም መለሰ፦ “እነሆ አያምኑኝም፤ ቃሌንም አይሰሙም፤ ‘እግዚአብሔር ከቶ አልተገለጠልህም’ ይሉኛል” አለ። እግዚአብሔርም፦ “ይህች በእጅህ ያለችው ምንድር ናት?” አለው። እርሱም፦ “በትር ናት፤” አለ። “ወደ መሬት ጣላት፤” አለው፤ እርሱም በመሬት ጣላት፤ እባብም ሆነች፤ ሙሴም ከእርሷ ሸሸ። እግዚአብሔርም ሙሴ፥ “የአባቶቻቸው አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ፥ እግዚአብሔር እንደ ተገለጠልህ እንዲያምኑ እጅህን ዘርግተህ ጅራትዋን ያዝ፤” አለው። እጁንም ዘርግቶ ያዛት በእጁም ውስጥ በትር ሆነች። እግዚአብሔርም ደግሞ፦ “እጅህን ወደ ብብትህ አግባ፤” አለው። እጁንም ወደ ብብቱ አገባት፤ ባወጣትም ጊዜ እነሆ፥ እጁ እንደ በረዶ ለምጽ ሆነች። እርሱም፦ እጅህን ወደ ብብትህ መልስ አለው። እጁንም ወደ ብብቱ መለሳት፥ ከብብቱም ባወጣት ጊዜ እነሆ ተመልሳ ገላውን መሰለች። ደግሞም አለው፦ “እንዲህም ይሆናል፤ ባያምኑህ የፊተኛይቱንም ምልክት ነገር ባይሰሙ፥ የሁለተኛይቱን ምልክት ነገር ያምናሉ። እንዲህም ይሆናል፤ እነዚህን ሁለት ምልክቶች ባያምኑ ቃልህንም ባይሰሙ፥ ከወንዙ ውኃን ውሰድ፤ በደረቁም መሬት ላይ አፍስሰው፤ ከወንዙም የወሰድኸው ውኃ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል።” ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “ጌታ ሆይ! እኔ አፌ ኮልታፋ ምላሴም ጸያፍ የሆነ ሰው ነኝ፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባሪያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይደለሁም።” እግዚአብሔርም፦ “የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕውርስ ያደረገ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? እንግዲህ አሁን ሂድ፤ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፤ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ፤” አለው። እርሱም፦ “ጌታ ሆይ! በምትልከው ሰው እጅ ትልክ ዘንድ እለምንሃለሁ፤” አለ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}