የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘጸአት 2:15-18

ኦሪት ዘጸአት 2:15-18 አማ54

ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፤ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ በውኃም ጉድጓድ አጠገብ ዐረፈ። ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም በጎች ሊያጠጡ የውኃውንም ገንዳ ሞሉ። እረኞችም መጥተው ገፉአቸው፤ ሙሴ ግን ተነሥቶ ረዳቸው፤ በጎቻቸውንም አጠጣላቸው። ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤልም በመጡ ጊዜ፦ “ስለ ምን ዛሬ ፈጥናችሁ መጣችሁ?” አላቸው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}