የሐዋርያት ሥራ 8:27-31

የሐዋርያት ሥራ 8:27-31 አማ54

ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። መንፈስም ፊልጶስን፦ “ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ” አለው። ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና፦ “በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው። እርሱም፦ “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።