የሐዋርያት ሥራ 13:49-52

የሐዋርያት ሥራ 13:49-52 አማ54

የጌታም ቃል በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ። አይሁድ ግን የሚያመልኩትን የከበሩትንም ሴቶችና የከተማውን መኳንንት አወኩ፥ በጳውሎስና በበርናባስም ላይ ስደትን አስነሥተው ከአገራቸው አወጡአቸው። እነርሱ ግን የእግራቸውን ትቢያ አራግፈውባቸው ወደ ኢቆንዮን መጡ። በደቀ መዛሙርትም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው።