ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:1-4

ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 20:1-4 አማ54

እንዲህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞዓብና የአሞን ልጆች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሳፍጥን ሊወጉ መጡ። ወሬኞችም መጥተው “ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም፥ ዓይንጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ናቸው” ብለው ለኢዮሳፍጥ ነገሩት። ኢዮሳፍጥም ፈራ፤ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ። ይሁዳም እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ተከማቸ፤ ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ መጡ።