አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 22:37-39

አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 22:37-39 አማ54

ወደ ሰማርያም መጡ፤ ንጉሡንም በሰማርያ ቀበሩት። አመንዝሮች በታጠቡባት በሰማርያ ኩሬ ሠረገላውን አጠቡት፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ቃል ውሾች ደሙን ላሱት። የቀረውም የአክዓብ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የሠራው ቤት፥ የሠራቸውም ከተሞች ሁሉ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?