አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:22-24

አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:22-24 አማ54

ኤልያስም ሕዝቡን አለ “ከእግዚአብሔር ነቢያት እኔ ብቻ ቀርቻለሁ፤ የበኣል ነቢያት ግን አራት መቶ አምሳ ሰዎች ናቸው። ሁለት ወይፈኖች ይሰጡን፤ እነርሱም አንድ ወይፈን ይምረጡ፤ በየብልቱም ይቁረጡት፤ በእንጨትም ላይ ያኑሩት፤ በበታቹም እሳት አይጨምሩ፤ እኔም ሁለተኛውን ወይፈን አዘጋጃለሁ፤ በእንጨቱም ላይ አኖረዋለሁ፤ በበታቹም እሳት አልጨምርም። እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ “ይህ ነገር መልካም ነው፤” ብለው መለሱ።