አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 6
6
የሊቀ ካህናት ቤተሰብ የትውልድ ሐረግ
1የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። 2የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። 3የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር። 4አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ 5አቢሱም ቡቂን ወለደ፤ ቡቂም ኦዚን ወለደ፤ 6ኦዚም ዘራእያን ወለደ፤ ዘራእያም መራዮትን ወለደ፤ 7መራዮት አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 8አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማአስን ወለደ፤ 9አኪማአስም ዓዛርያስን ወለደ፤ ዓዛርያስም ዮሐናንን ወለደ፤ 10ዮሐናንም ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በሠራው ቤት ካህን ነበረ፤ 11ዓዛርያስም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 12አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም ሰሎምን ወለደ፤ 13ሰሎምም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስም ዓዛርያስን ወለደ፤ 14ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤ 15እግዚአብሔርም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን በናቡከደነፆር እጅ ባስማረከ ጊዜ ኢዮሴዴቅ ተማርኮ ሄደ።
የሌዊ ትውልድ
16የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። 17የጌድሶንም ልጆች ስም ይህ ነው፤ ሎቤኒ ሰሜኢ። 18የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ። 19የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። 20ከጌድሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፥ 21ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ። 22የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፥ 23ልጁ ሕልቃና፥ ልጁ አቢሳፍ፥ ልጁ አሴር፥ 24ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኡርኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል። 25የሕልቃናም ልጆች፤ አማሢ፥ አኪሞት። 26የሕልቃናም ልጆች፤ ልጁ ሱፊ፥ ልጁ ናሐት፥ 27ልጁ ኤልያብ፥ ልጁ ይሮሐም፥ ልጁ ሕልቃና። 28የሳሙኤልም ልጆች፤ በኵሩ ኢዮኤል፥ ሁለተኛውም አብያ። 29የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ሰሚኢ፥ ልጁ ዖዛ፥ 30ልጁ ሳምዓ፥ ልጁ ሐግያ፥ ልጁ ዓሣያ።
የቤተ መቅደስ መዘምራን
31ዳዊትም ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በእግዚአብሔር ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው። 32ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር። 33አገልጋዮቹና ልጆቹ እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዮኤል ልጅ፥ የሳሙኤል ልጅ፥ 34የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥ 35የሱፍ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የመሐት ልጅ፥ 36የአማሢ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የኢዮኤል ልጅ፥ የዓዛርያስ ልጅ፥ የሶፎንያስ ልጅ፥ 37የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥ የአብያሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥ 38የይስዓር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነው። 39በቀኙም የቆመ ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥ የሳምዓ ልጅ፥ 40የሚካኤል ልጅ፥ የበዓሤያ ልጅ፥ የመልክያ ልጅ፥ 41የኤትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ 42የኤታን ልጅ፥ የዛማት ልጅ፥ የሰሜኢ ልጅ፥ 43የያሐት ልጅ፥ የጌድሶን ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነው። 44በግራቸውም በኩል ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥ የማሎክ ልጅ፥ 45የሐሸብያ ልጅ፥ የአሜስያስ ልጅ፥ የኬልቅያስ ልጅ፥ 46የአማሲ ልጅ፥ የባኒ ልጅ፥ የሴሜር ልጅ፥ 47የሞሖሊ ልጅ፥ የሙሲ ልጅ፥ የሜራሪ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ። 48ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ።
የአሮን ትውልድ
49አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሠርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፤ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር። 50የአሮንም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ልጁ አልዓዛር፥ ልጁ ፊንሐስ፥ ልጁ አቢሱ፥ 51ልጁ ቡቂ፥ ልጁ ኦዚ፥ ልጁ ዘራእያ፥ 52ልጁ መራዮት፥ ልጁ አማርያ፥ ልጁ አኪጦብ፥ 53ልጁ ሳዶቅ፥ ልጁ አኪማአስ።
ለሌዋውያን የተሰጡ መኖሪያ ስፍራዎች
54ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ። 55ለእነርሱ በይሁዳ አገር ያለችውን ኬብሮንን፥ በእርስዋ ዙሪያ የነበረውን መሰማርያ ሰጡ፤ 56የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጡ። 57ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰምርያዋን፥ ደግሞ የቲርን፥ ኤሽትሞዓንና መሰማርያዋን፥ 58ሖሎንንና መሰማርያዋን፥ ዳቤርንና መሰማርያዋን፥ 59ዓሳንንና መሰማርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰማርያዋን፤ 60ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማርያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማርያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
61ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከነገዱ ወገን ከምናሴ ነገድ እኵሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 62ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ። 63ለሜራሪ ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 64የእስራኤልም ልጆች ለሌዋውያን ከተሞችን ከመሰማርያዎቻቸው ጋር ሰጡ። 65ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ።
66ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው። 67በተራራማው በኤፍሬም አገር ያሉትን የመማፀኛውን ከተሞች ሴኬምንና መሰማርያዋን፥ ደግሞም ጌዝርንና መሰማርያዋን፥ 68ዮቅምዓምንና መሰማርያዋን፥ ቤትሖሮንንና መሰማርያዋን፥ 69ኤሎንንና መሰምርያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን ሰጡአቸው። 70ከምናሴም ነገድ እኵሌታ ዓኔርንና መሰማርያዋን፥ ቢልዓምንና መሰማርያዋን፥ ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ።
71ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኵሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጎላንና መሰማርያዋ፥ አስታሮትና መሰማርያዋ፤ 72ከይሳኮርም ነገድ ቃዴስና መሰማርያዋ፥ ዳብራትና መሰማርያዋ፥ 73ራሞትና መሰማርያዋ፥ ዓኔምና መሰማርያዋ፤ 74ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰማርያዋ፥ ዓብዶንና መሰማርያዋ፥ 75ሑቆቅና መሰማርያዋ፥ ረአብና መሰማርያዋ፤ 76ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማርያዋ፥ ሐሞንና መሰማርያዋ፥ ቂርያታይምና መሰማርያዋ ተሰጡ።
77ከሌዋውያን ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ከዛብሎን ነገድ ሬሞንና መሰማርያዋ፥ ታቦርና መሰማርያዋ፤ 78ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰማርያዋ፥ ያሳና መሰማሪያዋ፥ 79ቅዴሞትና መሰማርያዋ፥ ሜፍዓትና መሰማርያዋ፤ 80ከጋድም ነገድ በገለዓድ ያለችው ሬማትና መሰምርያዋ፥ መሃናይምና መሰማርያዋ፥ 81ሐሴቦንና መሰምርያዋ፥ ኢያዜርና መሰማርያዋ ተሰጡ።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 6: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ