የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መሓ​ልየ መሓ​ልይ ዘሰ​ሎ​ሞን 7

7
1አንቺ ሱላ​ማ​ጢስ ሆይ፥ ተመ​ለሽ፥ ተመ​ለሽ፤
እና​ይ​ሽም ዘንድ ተመ​ለሽ፥ ተመ​ለሽ።
በሱ​ላ​ማ​ጢስ ምን ታያ​ላ​ችሁ?
እር​ስዋ በሩቁ እን​ደ​ም​ት​ታይ እንደ ማኅ​በር ማሕ​ሌት ናት።
2አንቺ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ሆይ፥
በጫማ አካ​ሄ​ድሽ እጅግ ያማረ ነው።
የዳ​ሌ​ዎ​ችሽ አቀ​ማ​መጥ በአ​ን​ጥ​ረኛ እጅ እንደ ተሠሩ
እንደ ዕን​ቍ​ዎች ይመ​ስ​ላል።
3እን​ብ​ር​ትሽ የወ​ይን ጠጅ እን​ደ​ማ​ይ​ጐ​ድ​ል​በት እንደ ተነ​ጠጠ ጽዋ ነው፤
ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር፥ በአ​በ​ባም እንደ ታጠረ ነው።
4ሁለቱ ጡቶ​ችሽ እንደ ሁለት መንታ
እንደ ሚዳቋ ግል​ገ​ሎች ናቸው።
5አን​ገ​ትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፤
ዐይ​ኖ​ችሽ በሐ​ሴ​ቦን ውስጥ በብ​ዙ​ዎች ልጅ በሮች አጠ​ገብ እን​ዳሉ
እንደ ውኃ ኵሬ​ዎች ናቸው፤
አፍ​ን​ጫሽ ወደ ደማ​ስቆ አፋ​ዛዥ እን​ደ​ሚ​መ​ለ​ከት
እንደ ሊባ​ኖስ ግንብ ነው።
6በራ​ስሽ ላይ ያለው ጠጕ​ርሽ እንደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ነው፤
የጠ​ጕ​ር​ሽም ሹርባ እንደ ሐም​ራዊ ሐር ነው፥
ንጉ​ሡም በሹ​ር​ባው ታስ​ሯል።#ግእዝ “አሠረ ንጉሥ ለረ​ዊጽ” ይላል።
7ወዳጄ ሆይ፥ እን​ዴት የተ​ዋ​ብሽ ነሽ!
እን​ዴ​ትስ ደስ ታሰ​ኛ​ለሽ!
ደስ​ታ​ሽ​ንም እወ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ።
8ይህ ቁመ​ትሽ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ይመ​ስ​ላል፥
ጡቶ​ች​ሽም የወ​ይን ዘለላ ይመ​ስ​ላሉ።
9ወደ ዘን​ባ​ባው ዛፍ እወ​ጣ​ለሁ
ጫፉ​ንም እይ​ዛ​ለሁ አልሁ፤
ጡቶ​ችሽ እንደ ወይን ዘለላ ናቸው፥
የአ​ፍ​ን​ጫ​ሽም ሽታ እንደ እን​ኮይ ነው።
10ጕሮ​ሮ​ሽም ለልጅ ወን​ድሜ እየ​ጣ​ፈጠ እን​ደ​ሚ​ገባ፥
ለከ​ን​ፈ​ሮ​ችና ለም​ላሴ እን​ደ​ሚ​ስ​ማማ
እንደ ማለ​ፊያ የወ​ይን ጠጅ ነው።
11እኔ የልጅ ወን​ድሜ ነኝ፥ የእ​ር​ሱም መመ​ለ​ሻው#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ምኞቱ” ይላል። ወደ እኔ ነው።
12ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እን​ውጣ፥
በመ​ን​ደ​ሮ​ችም እን​ደር።
13ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፤
ወይኑ አብቦ፥ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ
ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤
በዚያ ጡቶቼን እሰጥሃለሁ።
14ትርንጎዎች መዓዛን ስጡ፤
መልካሞች ፍሬዎች ሁሉ፥
አሮጌው ከአዲሱ ጋር፥ በደጃችን አሉ፤
ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ሁሉን ለአንተ ጠበቅሁልህ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ