የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መሓ​ልየ መሓ​ልይ ዘሰ​ሎ​ሞን 1:1-6

መሓ​ልየ መሓ​ልይ ዘሰ​ሎ​ሞን 1:1-6 አማ2000

ከመ​ዝ​ሙር ሁሉ የሚ​በ​ልጥ የሰ​ሎ​ሞን መዝ​ሙር። በአፉ አሳ​ሳም ይስ​መ​ኛል፥ ጡቶ​ችሽ ከወ​ይን ይልቅ ያማሩ ናቸው። የሽ​ቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ሽቱ ነው፤ ስለ​ዚህ ደና​ግል ወደ​ዱህ። ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤ ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤ አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው። እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድን​ኳ​ኖች እንደ ሰሎ​ሞ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች። ፀሓይ መል​ኬን አክ​ስ​ሎ​ታ​ልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አት​ዩኝ፤ የእ​ናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ች​ንም ጠባቂ አደ​ረ​ጉኝ፤ ነገር ግን የእ​ኔን የወ​ይን ቦታ አል​ጠ​በ​ቅ​ሁም።