መጽ​ሐፈ ሲራክ 10

10
1ጠቢብ ንጉሥ ሕዝ​ቡን ይመ​ክ​ራል፥
አስ​ተ​ዋይ ዳኛም ሥር​ዐ​ትን ይሠ​ራል።
2ሎሌ​ውም እንደ ሕዝቡ አለቃ ነው፤
የከ​ተ​ማው ገዥ እን​ደ​ሚ​ሠ​ራው በው​ስጧ የሚ​ኖሩ ሰዎች ይሠ​ራሉ።
3አላ​ዋቂ ንጉሥ ሕዝ​ቡን ያጠ​ፋል፤
ሀገ​ርም በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጥበብ ትጸ​ና​ለች።
4የም​ድር ግዛት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ነው፥
በጊ​ዜ​ውም የሚ​ጠ​ቅ​መ​ውን ሰው በእ​ር​ስዋ ላይ ያስ​ነ​ሣል።
5የሰው በረ​ከቱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ነው፥
በጸ​ሓ​ፊም ሰው​ነት ክብ​ሩን ያኖ​ራል።
በት​ዕ​ቢት የሚ​መጣ ኀጢ​አት
6ባል​ን​ጀ​ራ​ህን በሳ​ተ​በት ሁሉ አት​ን​ቀ​ፈው፥
በነ​ቀ​ፋ​ህም ምንም ክፉ ነገር የም​ታ​ደ​ር​ግ​በት አይ​ኑር።
7ትዕ​ቢት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሰው ዘንድ የተ​ጠላ ነው፥
ከሁ​ሉም ዐመፅ ትከ​ፋ​ለች።
8መን​ግ​ሥ​ትም ስለ ዐመ​ፅና ክር​ክር፥ ስለ ገን​ዘ​ብም፥
ካንዱ ወገን ወደ ሌላው ወገን ትፈ​ል​ሳ​ለች።
9እን​ግ​ዲህ ትቢ​ያና ዐመድ የሚ​ሆን፥
በሕ​ይ​ወ​ትም ሳለ ሰው​ነቱ የሚ​ተላ ሰው ለምን ይታ​በ​ያል?
10የሰፋ ቍስ​ልን ባለ መድ​ኀ​ኒት ያድ​ነ​ዋል፤
ንጉሥ መባል ግን ለዛሬ ብቻ ነው፥ ነገም ይሞ​ታል።
11ሰውም ከሞተ በኋላ የትል ዕድል ፋንታ ይሆ​ናል።
12የት​ዕ​ቢት መጀ​መ​ሪያ ሰውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትለ​የ​ዋ​ለች፤
ልቡ​ና​ው​ንም ከፈ​ጣ​ሪው ታር​ቀ​ዋ​ለች።
13ትዕ​ቢት የኀ​ጢ​አት መጀ​መ​ሪያ ናት፤
በአ​ጸ​ና​ትም ሰው ላይ ርኵ​ሰ​ትን ታበ​ዛ​በ​ታ​ለች፥
ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ፍዳ ይገ​ል​ጣል፥
ፈጽ​ሞም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ቆ​ችን ዙፋን ያፈ​ር​ሳል፤
በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ የዋ​ሃ​ንን ይሾ​ማል።
15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሕ​ዛ​ብን ሥራ​ቸ​ውን ነቀለ፥
በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ ትሑ​ታ​ንን ተከለ።
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሕ​ዛ​ብን ሀገ​ሮች አጠፋ፥
እስከ ምድር መሠ​ረት ድረስ አጠ​ፋ​ቸው።
17ፈጽ​ሞም አጠ​ፋ​ቸው፥
ስም አጠ​ራ​ራ​ቸ​ው​ንም ከም​ድር ደመ​ሰሰ።
18ትዕ​ቢት ለሰው የተ​ፈ​ጠረ አይ​ደ​ለም፥
ቍጣና ጥፋ​ትም ከሴት ለሚ​ወ​ለድ ሰው አይ​ደ​ለም።
ክብር ስለ​ሚ​ገ​ባ​ቸ​ውና ስለ​ማ​ይ​ገ​ባ​ቸው
19የሰው ዘር የከ​በረ ዘር ነው፥
የከ​በረ ዘር ማን​ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሰዎች ዘር አይ​ደ​ለ​ምን?
20የሰው ዘር የጐ​ሰ​ቈለ ዘር ነው፥
ጐስ​ቋ​ላው ዘር ማን​ነው? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ የማ​ይ​ጠ​ብቁ ሰዎች ዘር አይ​ደ​ለ​ምን?
21ዳኛ ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ይልቅ የከ​በረ ነው፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሰዎች ግን ከእ​ርሱ ይልቅ ይከ​ብ​ራሉ።
22ለባ​ለ​ጸ​ጋ​ውና ለከ​በ​ር​ቴው ለድ​ሃ​ውም
ክብ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ነው።
23ድሃ​ውን ስለ ድህ​ነቱ ይን​ቁት ዘንድ አይ​ገ​ባም፥
ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ው​ንም ሰው ስለ ባለ​ጸ​ግ​ነቱ ያከ​ብ​ሩት ዘንድ አይ​ገ​ባም።
24ታላ​ላ​ቆ​ችና አለ​ቆች፥ መኳ​ን​ን​ቱም ይከ​ብ​ራሉ፤
ከእ​ነ​ር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰውን የሚ​በ​ል​ጠው የለም።
25ጠቢብ ቤተ ሰብ በን​ጹሕ ያገ​ለ​ግ​ላል፥
ዐዋቂ ሰውም አይ​ነ​ቅ​ፈ​ውም።
26ሥራ​ህን ስት​ሠራ አት​ራ​ቀቅ፥
በች​ግ​ር​ህም ወራት አት​መካ።
27ከሚ​ዞ​ርና ከሚ​መካ፥ ምግ​ቡ​ንም ከማ​ያ​ገኝ ሰው ይልቅ፥
የሚ​ያ​ር​ስና የሚ​ቈ​ፍር ይሻ​ላል።
28ልጄ ሆይ፥ በየ​ዋ​ህ​ነ​ትህ ሰው​ነ​ት​ህን ደስ አሰ​ኛት፥
የተ​ቻ​ለ​ህ​ንም ያህል አዘ​ጋ​ጃት።
29ለራሱ የሚ​ነ​ፍግ ለማን ቸር ይሆ​ናል?#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በራሱ ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ራን ሰው ማን ንጹሕ ያደ​ር​ገ​ዋል? ራሱን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ው​ንስ ማን ያከ​ብ​ረ​ዋል” ይላል።
ሰው​ነ​ቱን የማ​ያ​ዘ​ጋ​ጃ​ትን ሰውስ ማን ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል?
30ድሃ​ውን ስለ ጥበቡ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፥
ባለ​ጠ​ጋ​ውን ግን ስለ ባለ​ጠ​ግ​ነቱ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
31በተ​ቸ​ገረ ጊዜ የማ​ያ​ዝን ሰው፥
በተ​ዘ​ጋጀ ጊዜ እን​ዴት ደስ ይለው?#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በተ​ቸ​ገረ ጊዜ የተ​ከ​በረ ሰው በበ​ለ​ጸገ ጊዜ ምን ያህል ይከ​ብር ይሆን? በበ​ለ​ጸ​ገ​በት ጊዜ የተ​ዋ​ረ​ደስ በተ​ቸ​ገረ ጊዜ ምን ያህል ይዋ​ረድ ይሆን?” ይላል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ