ወደ ሮሜ ሰዎች 16
16
1ለክንክራኦስ ቤተ ክርስቲያን የምትላላከውን እኅታችንን ፌቤንን አደራ እላችኋለሁ፤ 2ለቅዱሳንም እንደሚገባ በጌታችን ተቀበሉአት፤ እርስዋ ለብዙዎች፥ ለእኔም ረዳት ናትና፤ ለችግራችሁም በፈቀዳችሁት ቦታ መድቡአት።#ግሪኩ እና አንዳንድ የግእዝ ዘርዕ “ከእናንተ በምትፈልገው በማንናውም ነገር ርዱአት” ይላል።
3 #
የሐዋ. 18፥2። በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ከእኔ ጋር የተባበሩትን ጵርስቅላንና አቂላን ሰላም በሉ፤ 4ስለ እኔ ሰውነታቸውን ለመከራ አሳልፈው ሰጥተዋልና፤ የማመሰግናቸውም እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ከአሕዛብ ያመኑ ምእመናን ሁሉ ያመሰግኑአቸዋል እንጂ። 5በቤታቸው ያሉትን ማኅበረ ክርስቲያንም ሰላም በሉ፤ ወዳጄ ኤጴኔጦስንም እንዴት ነህ? በሉ፤ ይኸውም በእስያ በክርስቶስ ላመኑ ሁሉ መጀመሪያቸው ነው። 6ለእናንተ ብዙ የደከመችላችሁን ማርያምንም ሰላም በሉ። 7ከዘመዶች ወገን የሚሆኑትን ከእኔ ጋር ያመኑ እንድራናቆስንና ዩልያንን ሰላም በሉ፤ ቀደም ሲል ክርስቶስን እንደ አገለገሉ ሐዋርያት ያውቁአቸዋል። 8በክርስቶስ ወንድሜ የሆነውን አምጵልያጦስን ሰላም በሉ። 9የክርስቶስን ሥራ በመሥራት የምንተባበረውን ኡሩባኖስን፥ ወዳጄ ስንጣክንንም ሰላም በሉ። 10በክርስቶስ የተመረጠውን ኤጤሌንን ሰላም በሉ፤ እነ አርስጠቦሎስንም ሰላም በሉ። 11ከዘመዶች ወገን የሚሆን ሄሮድዮናን ሰላም በሉ፤ በንርቃሶስ ቤት ያሉትንና በክርስቶስ ያመኑትን ምእመናን ሰላም በሉ። 12በጌታችን ስም መከራ የተቀበሉትን የጢሮፊሞናንና የጢሮፊሞስን ወገኖች ሰላም በሉ። በጌታችን ስም ብዙ የደከመች እኅታችንን ጠርሴዳን ሰላም በሉ። 13#ማር. 15፥21። ጌታችን የመረጠው ሩፎንን፥ እናቱንም፥ ለእኔም እናቴ የሆነችውን ሰላም በሉ። 14አስቀሪጦስን፥ አልሶንጳን፥ ሄርሜስን፥ ጳጥሮባስን፥ ሄርማስን፥ ከእነርሱ ጋር ያሉ ወንድሞቻችንንም ሰላም በሉ። 15ፊሎሎጎስን፥ ዩልያን፥ ኔርዮስን፥ እኅቱንም አሊንጳስን ከእነርሱም ጋር ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ ሰላም በሉ። 16እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ ሰላምታ ሰላም ተባባሉ፤ የክርስቶስ ማኅበረ ክርስቲያንም ሰላም ይሉአችኋል።
17ወንድሞቻችን ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን፥ መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን እንድታውቁባቸው እማልዳችኋለሁ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ 18እነርሱ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያይደለ ለሆዳቸው ይገዛሉና፤ በነገር ማታለልና በማለዛዘብም የብዙዎች የዋሃንን ልብ ያስታሉ፤ 19መታዘዛችሁም በሁሉ ዘንድ ተሰምቶአል፤ እኔም በእናንተ ደስ ይለናል፤ ለመልካም ነገር ጠቢባን፥ ለክፉ ነገርም የዋሃን እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። 20የሰላም አምላክም ፈጥኖ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ይቀጥቅጠው፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።
21 #
የሐዋ. 16፥1። ከእኔ ጋር በሥራ የሚተባበረው ጢሞቴዎስም፥ ከዘመዶች ወገን የሚሆኑ ሉቅዮስም፥ ኢያሶንም፥ ሱሲ ጴጥሮስም ሰላም ይሉአችኋል። 22ይህችን መልእክት የጻፍኋት እኔ ጤርጥዮስ በጌታችን ስም ሰላም እላችኋለሁ። 23#የሐዋ. 19፥29፤ 1ቆሮ. 1፥14፤ 2ጢሞ. 4፥20። እኔንና አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ በእንግድነት የተቀበለ ጋይዮስም ሰላም ብሎአችኋል፤ የከተማው መጋቢ አርስጦስና ወንድማችን ቁአስጥሮስም ሰላም ብለዋችኋል። 24ከዓለም አስቀድሞ ምሥጢሩ ተሰውሮ ስለ ነበረ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በማስተምራት ትምህርት ላይ ሊያጸናችሁ የሚችለው እርሱ እግዚአብሔር ነው።
25ይህም በነቢያት ቃልና የዘለዓለም ገዥ በሚሆን በእግዚአብሔር ትእዛዝ በዚህ ወራት ተገለጠ፤ አሕዛብ ሁሉ ይህን ሰምተውና ዐውቀው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ። 26ብቻውን ጠቢብ ለሆነው ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን፤ አሜን። 27የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።
በቆሮንቶስ ተጽፋ ለክንክራኦስ ማኅበረ ክርስቲያን በምትላላከው በፌቤን እጅ ወደ ሮሜ ሰዎች የተላከችው መልእክት ተፈጸመች።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች 16: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ