የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ሮሜ ሰዎች 15

15
ባል​ን​ጀ​ራን ስለ መር​ዳት
1የሚ​ገ​ባስ እና ብር​ቱ​ዎች ደካ​ሞ​ችን በድ​ካ​ማ​ቸው እን​ድ​ን​ረ​ዳ​ቸው ነው፤ ለራ​ሳ​ች​ንም አና​ድላ። 2ሁላ​ች​ንም በእ​ው​ነ​ትና በመ​ል​ካም ሥራ ይታ​ነጽ ዘንድ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችን እና​ድላ። 3#መዝ. 68፥9። ክር​ስ​ቶ​ስም፥ “አን​ተን የነ​ቀ​ፉ​በት ነቀፋ በእኔ ላይ ደረሰ” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ ለራሱ ያደላ አይ​ደ​ለም። 4የተ​ጻ​ፈው ሁሉ በመ​ታ​ገ​ሣ​ች​ንና መጻ​ሕ​ፍ​ትን በመ​ታ​መ​ና​ችን ተስ​ፋ​ች​ንን እና​ገኝ ዘንድ እና ልን​ማ​ር​በት ተጻፈ። 5የት​ዕ​ግ​ሥ​ትና የመ​ጽ​ና​ናት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፈቃድ እርስ በር​ሳ​ችን አንድ ዐሳብ መሆ​ንን ይስ​ጠን። 6ሁላ​ችን አንድ ሆነን በአ​ንድ አፍ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ።#ምዕ. 15 ቍ. 5 እና 6 ግሪኩ በሁ​ለ​ተና መደብ ይጽ​ፋል።
ወን​ጌ​ልን ለአ​ሕ​ዛ​ብም ለአ​ይ​ሁ​ድም ስለ መስ​በክ
7አሁ​ንም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ተቀ​በሉ፤ ክር​ስ​ቶስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ተቀ​ብ​ሎ​አ​ች​ኋ​ልና። 8እን​ግ​ዲህ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እው​ነት ለማ​ድ​ረግ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም ተስፋ ያጸና ዘንድ ለግ​ዝ​ረት መል​እ​ክ​ተና ሆነ እላ​ለሁ። 9#2ሳሙ. 22፥50፤ መዝ. 17፥49። አሕ​ዛ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ይቅር ብሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “አቤቱ፥ ስለ​ዚህ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።” 10#ዘዳ. 32፥43። ዳግ​መ​ናም መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “አሕ​ዛብ ከሕ​ዝቡ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ።” 11#መዝ. 116፥1። ዳግ​መ​ናም እን​ዲህ አለ፥ “አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።” 12#ኢሳ. 11፥10። ኢሳ​ይ​ያ​ስም ደግሞ እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “የእ​ሴይ ዘር ይነ​ሣል፤ ከእ​ርሱ የሚ​ነ​ሣ​ውም ለአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ሕዝ​ቡም ተስፋ ያደ​ር​ጉ​ታል።” 13የተ​ስፋ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይል በተ​ስፋ ያበ​ዛ​ችሁ ዘንድ በእ​ም​ነት ደስ​ታ​ንና ሰላ​ምን ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ።
የጳ​ው​ሎስ ሐዋ​ር​ያዊ ተል​እኮ
14ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔም በጎ ምግ​ባ​ርን ሁሉ እን​ደ​ም​ት​ፈ​ጽሙ እታ​መ​ን​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ ፍጹም ዕው​ቀ​ትን የተ​መ​ላ​ችሁ ናችሁ፤ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም ልታ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ትች​ላ​ላ​ችሁ። 15ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አገ​ኘ​ሁት ጸጋ ላሳ​ስ​ባ​ችሁ በአ​ን​ዳ​ንድ ቦታ በድ​ፍ​ረት ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ። 16በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግል ዘንድ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወን​ጌ​ልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትም​ህ​ርት አሕ​ዛብ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የተ​ወ​ደ​ደና የተ​መ​ረጠ መሥ​ዋ​ዕት ይሆኑ ዘንድ። 17ለእ​ኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መመ​ኪ​ያዬ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው። 18አሕ​ዛ​ብም እን​ዲ​ያ​ምኑ ክር​ስ​ቶስ በቃ​ልም በሥ​ራም ያደ​ረ​ገ​ል​ኝን እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ። 19በኀ​ይ​ልና በተ​አ​ም​ራት፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይ​ልና ድንቅ ሥራን በመ​ሥ​ራ​ትም፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ጀምሬ እስከ እል​ዋ​ሪ​ቆን ድረስ እንደ አስ​ተ​ማ​ርሁ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስ​ንም ወን​ጌል ፈጽሞ እንደ ሰበ​ክሁ እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ። 20ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር ተጋሁ፤ ነገር ግን በሌላ መሠ​ረት ላይ እን​ዳ​ላ​ንጽ የክ​ር​ስ​ቶስ ስም ወደ ተጠ​ራ​በት አል​ሄ​ድ​ሁም። 21#ኢሳ. 52፥15። “ወሬው ያል​ደ​ረ​ሳ​ቸው ያው​ቁ​ታል፤ ያል​ሰ​ሙ​ትም ያስ​ተ​ው​ሉ​ታል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ ነው።
22 # ሮሜ 1፥13። ዘወ​ትር ወደ እና​ንተ ልመጣ እወ​ድድ ነበር፤ ነገር ግን ተሳ​ነኝ። 23አሁን ግን በዚህ ሀገር ሥራ​ዬን ስለ ጨረ​ስሁ፥ ከብዙ ጊዜም ጀምሮ ወደ እና​ንተ ልመጣ እተጋ ስለ ነበር፤ 24ወደ አስ​ባ​ንያ ስሄድ እግረ መን​ገ​ዴን ላያ​ችሁ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቀደም ብዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ደስ ካለኝ በኋ​ላም ከእ​ና​ንተ ወደ​ዚያ እሄ​ዳ​ለሁ።
ምእ​መ​ና​ንን ስለ መር​ዳት
25አሁን ግን ቅዱ​ሳ​ንን ለመ​ር​ዳት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄ​ዳ​ለሁ። 26#1ቆሮ. 16፥1-4። መቄ​ዶ​ን​ያና አካ​ይያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅዱ​ሳን መካ​ከል ላሉ ድሆች አስ​ተ​ዋ​ጽ​ፅኦ ለማ​ድ​ረግ ተባ​ብ​ረ​ዋ​ልና። 27#1ቆሮ. 9፥11። የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ሰለ​ሆነ በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሥራ አሕ​ዛ​ብን ከተ​ባ​በ​ሩ​አ​ቸው ለሰ​ው​ነ​ታ​ቸው በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸው ሊረ​ዱ​አ​ቸው ይገ​ባል። 28እን​ግ​ዲህ ይህን ፍሬ ጨር​ሼና አትሜ በእ​ና​ንተ በኩል ወደ አስ​ባ​ንያ እሄ​ዳ​ለሁ። 29ነገር ግን በመ​ጨ​ረሻ ጊዜ በክ​ር​ስ​ቶስ ወን​ጌል በረ​ከት ፍጹ​ም​ነት እን​ደ​ም​ት​መጣ አም​ና​ለሁ።
30ወን​ድ​ሞች፥ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ስለ እኔ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ትተጉ ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ፍቅር እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። 31ይኸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ ቅዱ​ሳ​ንን በአ​ገ​ል​ግ​ሎቴ ደስ አሰ​ና​ቸው ዘንድ በይ​ሁዳ ሀገር ካሉ ዐላ​ው​ያን እን​ዲ​ያ​ድ​ነኝ ነው። 32እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቢፈ​ቅድ በደ​ስታ ወደ እና​ንተ መጥቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ዐርፍ ዘንድ ነው። 33የሰ​ላም አም​ላክ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ