የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ሮሜ ሰዎች 14

14
ባል​ን​ጀ​ራን ስለ ማጽ​ና​ናት
1እም​ነቱ ደካማ የሆ​ነ​ውን ሰው ታገ​ሡት፤ በዐ​ሳ​ቡም አት​ፍ​ረዱ። 2ሁሉን ይበላ ዘንድ እንደ ተፈ​ቀ​ደ​ለት የሚ​ያ​ምን ሁሉን ይብላ፤ የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን አት​ክ​ልት ይብላ። 3የሚ​በ​ላ​ውም የማ​ይ​በ​ላ​ውን አይ​ና​ቀው፤ የማ​ይ​በ​ላ​ውም የሚ​በ​ላ​ውን አይ​ን​ቀ​ፈው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አው​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና።#ግሪኩ “ተቀ​ብ​ሎ​ታ​ልና” ይላል። 4እን​ግ​ዲህ የሌ​ላ​ውን ሎሌ የም​ት​ነ​ቅፍ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወ​ድቅ ለጌ​ታው ነው። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ነ​ሣው ይች​ላ​ልና ይቆ​ማል።
5ከቀን ቀን የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ዘወ​ት​ርም የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ነገር ግን ሁሉም ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ።#ምዕ. 14 ቍ. 5 ከግ​ሪኩ ይለ​ያል። 6#ቈላ​. 2፥16። አን​ዳ​ንድ ቀን የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤#ግሪኩ “ቀንን የሚ​ያ​ከ​ብር ለጌታ ብሎ ያከ​ብ​ራል” ይላል። ዘወ​ትር የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤#“ዘወ​ትር የተ​ከ​ለ​ከለ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። የበ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፤ ያል​በ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​በ​ላም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል። 7ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም ለራሱ የሚ​ኖር፥ ለራ​ሱም የሚ​ሞት የለም። 8በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ኖ​ራ​ለን፤ ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ግ​ዲህ በሕ​ይ​ወት ብን​ኖ​ርም ብን​ሞ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነን። 9ስለ​ዚህ ሕያ​ዋ​ን​ንና ሙታ​ንን ይገዛ ዘንድ ክር​ስ​ቶስ ሞተ፥ ተነ​ሣም።
10 # 2ቆሮ. 5፥10። እን​ግ​ዲህ በወ​ን​ድ​ምህ ላይ የም​ት​ፈ​ርድ አንተ ምን​ድን ነህ? ወን​ድ​ም​ህ​ንስ የም​ት​ነ​ቅፍ አንተ ምን​ድን ነህ? ሁላ​ችን በክ​ር​ስ​ቶስ#አን​ዳ​ንድ የግ​ሪክ ዘርዕ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ይላል። የፍ​ርድ ዙፋን ፊት እን​ቆ​ማ​ለ​ንና። 11#ኢሳ. 45፥23። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “እኔ ሕያው ነኝ፤ ጕል​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይሰ​ግ​ዳል፤ አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይገ​ዛል።” 12እነሆ፥ ሁላ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​ደ​ም​ን​መ​ረ​መር ታወቀ።
ለባ​ል​ን​ጀራ ዕን​ቅ​ፋት ስላ​ለ​መ​ሆን
13እን​ግ​ዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በር​ሳ​ችን አን​ነ​ቃ​ቀፍ፤ ይል​ቁ​ንም ለወ​ን​ድም እን​ቅ​ፋ​ትን ወይም ማሰ​ና​ከ​ያን ማንም እን​ዳ​ያ​ኖር ይህን ዐስቡ። 14በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እን​ደ​ሌለ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ሆኜ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ተረ​ድ​ቼ​አ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን ማና​ቸ​ውም ነገር ርኩስ እን​ደ​ሚ​ሆን ለሚ​ያ​ስብ ያ ለእ​ርሱ ርኩስ ነው። 15በመ​ብል ምክ​ን​ያት ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ታ​ሳ​ዝን ከሆ​ንህ ፍቅር የለ​ህም፤ በውኑ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ሰው በመ​ብል ምክ​ን​ያት ሊጐዳ ይገ​ባ​ልን? 16እን​ግ​ዲህ ጌታ​ችን የሰ​ጠ​ንን መል​ካ​ሙን ነገር አታ​ሰ​ድቡ። 17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ጽድ​ቅና ሰላም፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የሆነ ደስታ ነው እንጂ መብ​ልና መጠጥ አይ​ደ​ለ​ምና። 18እን​ዲህ አድ​ርጎ ለክ​ር​ስ​ቶስ የሚ​ገዛ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝና በሰ​ውም ዘንድ የተ​መ​ረጠ ነው። 19አሁ​ንም ወን​ድ​ማ​ችን ይታ​ነጽ ዘንድ ሰላ​ምን እን​ከ​ተ​ላት።#በግ​ሪኩ “ሰላም የሚ​ቆ​ም​በ​ትን እርስ በር​ሳ​ች​ንም የም​ን​ታ​ነ​ጽ​በ​ትን እን​ከ​ተል” ይላል። 20በመ​ብል ምክ​ን​ያት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍጥ​ረት አና​ፍ​ርስ፤ ለን​ጹ​ሓን ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ለሰ​ውስ ክፉው ነገር በመ​ጠ​ራ​ጠር መብ​ላት ነው። 21ለወ​ን​ድም ዕን​ቅ​ፋት ከመ​ሆን ሥጋን አለ​መ​ብ​ላት ወይ​ን​ንም አለ​መ​ጠ​ጣት ይሻ​ላል። 22እም​ነት ካለህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባመ​ን​ኸው እም​ነት ራስ​ህን አጽና፤ ባገ​ኘው አእ​ም​ሮም ራሱን የሚ​ዘ​ልፍ ብፁዕ ነው።#ምዕ. 14 ቍ. 22 ግሪኩ “ለአ​ንተ ያለህ እም​ነት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለራ​ስህ ይሁ​ን​ልህ፤ ፈትኖ መል​ካም እን​ደ​ሚ​ሆን በሚ​ቈ​ጥ​ረው ነገር በራሱ ላይ የሚ​ፈ​ርድ ብፁዕ ነው” ይላል። 23የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን ቢበላ ይፈ​ረ​ድ​በ​ታል፤ በማ​መን አል​ሆ​ነ​ምና፤ ያለ እም​ነ​ትም የሚ​ደ​ረግ ሁሉ ኀጢ​አ​ትና በደል ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ